የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርና የማዕከላት ጉብኝት አካሄዱ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በዛሬው ዕለት የ2014 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አካሂደዋል፡፡
በተጨማሪም በደቡብ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በበጀት ዓመቱ እየተገነቡ የሚገኙ 17 ማዕከላት አካል የሆነውን የቦንጋ ከተማ አገልግሎት መስጫ ማዕከል የግንባታ ሂደት ጎብኝተዋል፡፡
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ስራውን በይፋ ሊጀምር መሆኑ ተገለፀ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያልተማከለ አደራጃጀት ተግባራዊ ባደረገው መሰረት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጽ/ቤት እንዳቋቋመና ከሐምሌ 1 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ በይፋ ስራውን እንደሚጀምር ተገልጿል፡፡
ይህ የተገለፀው ዛሬ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የቦርድ አባል አቶ ቦጋለ ፈለቀ፣ የአገልግሎቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሽፈራው ተሊላና ሌሎች የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች በርዕሰ መስተዳድሩ ቢሮ ባደረጉት የጋራ ስብሰባ ላይ ነው፡፡
በ162 ሚሊዮን ዶላር በላይ በሆነ ወጪ የተከናወነው የማሻሻያ ፕሮጀክት ተጠናቀቀ
በአዲስ አበባ ከተማ የሚስተዋለውን የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍ በ162 ሚሊዮን ዶላር በላይ በሆነ ወጪ ሲከናወን የቆየው የማሻሻያና መልሶ ግንባታ ፕሮጀክት የፊዚካል ስራ ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁን የፕሮጀክቱ ሃላፊ ወ/ሮ ቅድስት ላቀው ገልፀዋል፡፡
የመዲናዋን በፍጥነት ማደግንና የህብረተሰቡ የኃይል ፍላጎቱ ከመቼውም ጊዜ በላይ እየጨመረ መምጣቱን ተከተሎ ቀደም ሲል የነበረውን የኤሌክትሪክ መስመር እንደገና ማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ መቆየቱን ወ/ሮ ቅድስት አንስተዋል፡፡
ዲስትሪክቱ 43 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የመልሶ ግንባታ ስራ በማከናወን ላይ ይገኛል
በደቡብ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት የቦንጋ ዲስትሪክት ከተለያዩ የግል ሥራ ተቋራጮች ጋር በመተባበር 43 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የኤሌክትሪክ መስመር መልሶ ግንባታ ሥራ በማከናወን ላይ መሆኑን አስታውቋል፡፡
በዲስትሪክቱ የዲስትሪቡዩሽን፣ ኮንስትራክሽን፣ ኦፕሬሽንና ሜይቴናንስ ስራ አስኪያጅ አቶ እስራኤል ሀብታሙ እንደተናገሩት፡- ረጅም ዓመታት ያስቆጠሩ የኤሌክትሪክ ምሶሶዎች ከማርጀታቸው የተነሳ አገልግሎት መስጠት የማይችሉበት ደረጃ ላይ እየደረሱ በመሆኑ የመልሶ ግንባታ ሥራ ማከናወን አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የባቡር የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት የሰረቁ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ
ለአዲስ አበባ ከተማ ቀላል ባቡር የተዘረጉ የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማቶች ላይ የስርቆት ወንጀል ሲፈፅሙ የተገኙ 6 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ገልጷል፡፡
በአገልግሎቱ የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ማስተባበሪያ ሥራ አስኪያጅ አቶ ቢልቱማ ቂጣታ እንደገለፁት፡- ስርቆቱ የተፈፀመው ከሰኔ 14 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ 16 ቀን 2014 ዓ.ም ባሉት ቀናት ነው፡፡