የኮቪድ - 19 ስርጭት ለመግታት የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍ የ5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገ
የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል የሚያግዙ ቁሳቁሶች ድጋፍ ተደርገ
የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል የሚያግዙ ቁሳቁሶች ድጋፍ ተደርገ
የኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭትን ለመከላከል የሚያስችሉ የተለያዩ ውሳኔዎች ተላለፉ
ኢ.አር.ፒ
ተቋሙ የኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒንግ (ኢ.አር.ፒ) ፕሮጀክት አስመረቀ
ኢ.አር.ፒ
ተቋሙ የኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒንግ (ኢ.አር.ፒ) ፕሮጀክት አስመረቀ
ኢ.አር.ፒ
ተቋሙ የኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒንግ (ኢ.አር.ፒ) ፕሮጀክት አስመረቀ
ኢ.አር.ፒ
ተቋሙ የኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒንግ (ኢ.አር.ፒ) ፕሮጀክት አስመረቀ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የቴክኖሎጂ ማዕከል ለመገንባት የተደረገ የመግባቢያ ስምምነት በምስል /ህዳር 03 ቀን 2012 ዓ.ም/
በአዲሰ አበባ ግዮን ሆቴል የተካሄደው የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ በምስል/ ጥቅምት 25 ቀን 2012 ዓ.ም/
በኦሮሚያ ክልል ፊንፊኔ ልዩ ዞን አቃቂ ወረዳ ቆፍቱ ቀበሌ የተገነባው የሶላር ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በትናንትናው ዕለት መስከረም 9 ቀን 2012 ዓ.ም ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡
በቢሾፍቱ ሊሳክ ሪዞርት የተካሄደው የሚዲያ ኮሚዩኒኬሽን ፎረም በምስል /ጥቅምት 20 ቀን 2012 ዓ.ም/

ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሶስተኛው አመታዊ የሰራተኞች ቀን በዓል በድምቀት የተከበረው መጋቢት 26 ቀን 2011 ዓ.ም ጎፋ በሚገኘው የተቋሙ የስፖርት ሜዳ ነው፡59106228 2496527697025995 6038560899613065216 n

በክብረ በዓሉ የውሃ፣ መስኖ እና ኢነረጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ፣ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር እና የኢትዮጵያ ኤሌከልትሪክ አገልግሎት የቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር ጌታሁን መኩሪያ፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር አብረሃም በላይ፣ የኢትዮጵያ ኤሌከልትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፋጻሚ አቶ ሽፈራው ተሊላ እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

በዕለቱ የውሃ፣ መስኖ እና ኢነረጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ እና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ጌታሁን መኩሪያ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን፤ የውሃ፣ መስኖ እና ኢነረጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ ‹‹የኤሌክትሪክ አገልግሎት የሃገሪቱን የልማት እንቅስቃሴ የጀርባ አጥንት በመሆኑ ያለ ኤሌክትሪክ ምንም አይነት የልማት እንቅስቃሴ የማይታሰብ መሆኑን ገልፀው፤ ይህንን መተኪያ የሌለው የኢነርጂ ዘርፍ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በማስተሳሰር የአገልለግሎት አሰጣጡን ማሻሻልና ከህብረተሰቡ የሚነሱ ቅሬታዎችን መቀነስና የእረካታ ደረጃውን ከፍ ማድረግ እንደሚያስፍልግ አስገንዝበዋል››፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ጌታሁን መኩሪያ በበኩላቸው ‹‹እንደነዚህ አይነት ዝግጅቶች የሰራተኛውን የስራ ተነሳሽነት ለማሳደግ፣ የእርስ በእርስ ግንኙነት ለማጠናክር፣ ጤንነቱ የተጠበቀና ስራውን በኔነት ስሜት የሚሰራ ሠራተኛ ለመፍጠር ከፍተኛ አስተዋጾ እንዳላቸው ገልፀው፤ ሰራተኛው ተቋሙ የጀመራቸውን የስራ እንቅስቃሴዎች አጠናክሮ ማስቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል››፡፡

በዕለቱ የእግር ኳስ ጨዋታ፣ የደም ልገሳ፣ የሩጫ ውድድር፣ የእውቅናና ሽልማት ፕሮግራሞች የተከናወኑ ሲሆን፤ በመጀመሪያው መረሃ ግብር የሁለቱን እህት ድርጅቶች የእርስ በእርስ ግንኙነት ሊያጠናክር የሚችል የእግር ኳስ ውድድር በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል እና በኢትዮጵያ ኤሌከልትሪክ አገልግሎት ስራ አመራር አባላት መካከል ተካሂዶ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሁለት ጎል በማስቆጠር አሸናፊ ሆኗል፡፡

57414077 2496528060359292 5037868540808396800 n

በመቀጠል በኦሮሚያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አዘጋጅነት በአዳማ ከተማ በክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎቶች መካከል ሲከናወን በቆየው የእግር ኳስ ውድድር ለዋንጫ የደረሱት የትግራይና የሃረር ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎቶች የእግር ኳስ ቡድን አባላት ለዋንጫ የተጫወቱ ሲሆን፤ በውደድሩም የትግራይ ክልል የእግር ኳስ ቡድን በአሸናፊነት አጠናቋል፡፡

በዕለቱ 40 ዓመትና ከዚያ በላይ ተቋሙን አገልግለው በጡሮታ የተገለሉ ሰራተኞች የዕውቅና ምስጋና ሽልማት የተበረከተላቸው ሲሆን፤ በ1500 ሜትር የሩጫ ውድድር በሁለቱም ጾታዎች ተሳትፈው ለአሸናፊ ለሆኑ ተወዳዳሪዎች የዋንጫና የሜዳሊ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የመረብ ኳስ፣ የቼዝ፣ ዳማ፣ ቴነስ ውድድር አሽናፊዎች የሰርተፍኬትና የሜዳልያ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌከልትሪክ አገልግሎት ሰራተኞች የእግር ኳስ ውድድር በኦሮሚያ ክልል አዘጋጅነት በአዳማ ከተማ ሲካሄድ መቆየቱ የሚታወስ ነው፡፡

59267294 2496527747025990 2589599120364666880 n