የኮቪድ - 19 ስርጭት ለመግታት የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍ የ5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገ
የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል የሚያግዙ ቁሳቁሶች ድጋፍ ተደርገ
የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል የሚያግዙ ቁሳቁሶች ድጋፍ ተደርገ
የኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭትን ለመከላከል የሚያስችሉ የተለያዩ ውሳኔዎች ተላለፉ
ኢ.አር.ፒ
ተቋሙ የኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒንግ (ኢ.አር.ፒ) ፕሮጀክት አስመረቀ
ኢ.አር.ፒ
ተቋሙ የኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒንግ (ኢ.አር.ፒ) ፕሮጀክት አስመረቀ
ኢ.አር.ፒ
ተቋሙ የኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒንግ (ኢ.አር.ፒ) ፕሮጀክት አስመረቀ
ኢ.አር.ፒ
ተቋሙ የኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒንግ (ኢ.አር.ፒ) ፕሮጀክት አስመረቀ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የቴክኖሎጂ ማዕከል ለመገንባት የተደረገ የመግባቢያ ስምምነት በምስል /ህዳር 03 ቀን 2012 ዓ.ም/
በአዲሰ አበባ ግዮን ሆቴል የተካሄደው የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ በምስል/ ጥቅምት 25 ቀን 2012 ዓ.ም/
በኦሮሚያ ክልል ፊንፊኔ ልዩ ዞን አቃቂ ወረዳ ቆፍቱ ቀበሌ የተገነባው የሶላር ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በትናንትናው ዕለት መስከረም 9 ቀን 2012 ዓ.ም ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡
በቢሾፍቱ ሊሳክ ሪዞርት የተካሄደው የሚዲያ ኮሚዩኒኬሽን ፎረም በምስል /ጥቅምት 20 ቀን 2012 ዓ.ም/

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ ወርሀዊ የኤሌክትሪክ ኃይል ፍጆታ ክፍያን በአዲስ አበባ፣ በባህርዳር እና በመቀሌ ከተሞች በሚገኙ በ40 የለሁሉ የክፍያ ማዕከላት ሲያከናውን መቆየቱ ይታወቃል፡፡

በአሁን ወቅት ተቋሙ ለደንበኞቹ የሚሠጠውን አገልግሎት ለማቀላጠፍና ወርሃዊ የኃይል ፍጆታ ክፍያ ሥርዓትን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ ለማድረግ ዝግጅቱን ያጠናቀቀ ስለሆነ፤ በክፍያ ማዕከሉ ሲፈፀም የነበረውን የክፍያ ስርዓት ከሰኔ 26 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ እንዲቋረጥ ተወስኗል፡፡

 

65103523 2592925497386214 8052530872127062016 n

ለአፈፃፀሙም ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር የስምምነት ሰነድ የተፈረመ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም የከፍተኛና መካከለኛ ኃይል ተጠቃሚ ኢንዱስትሪዎች፣ የንግድ እንዲሁም መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ክፍያቸውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መፈፀም እንዲችሉ በየአገልግሎት መስጫ ማዕካላት ተገኝተው የውል ስምምነት እንዲፈፅሙ በድጋሚ እንገልፃለን፡፡ እነዚህ ደንበኞች በባንክ እንዲከፍሉ የተቀመጠው አሰራር እንደሚያስገድድ ልብ ይለዋል፡፡

ክፍያቸውን በባንክ ለመፈፀም ፍላጎቱ ያላቸው የመኖሪያ ቤት ደንበኞቻችንም በየአገልግሎት መስጫ ማዕከላት በመሄድ የውል ስምምነት እንዲፈፅሙ እንጠይቃለን፡፡

ሆኖም ለጊዜው ክፍያቸውን በባንክ ለመክፍል ያልተዘጋጁ የመኖሪያ ቤት ደንበኞቻችን፤ ከዚህ በፊት በለሁሉ የክፍያ ማዕከል ሲከናወን የነበረው የክፍያ ስርዓት ከሰኔ 26 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ የሚቋረጥ ስለሆነ፤ በአቅራቢያቸው በሚገኝ በየትኛውም የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት ወርሃዊ የፍጆታ ሂሳባቸውን መክፍል እንደሚችሉ እንገልፃለን፡፡

አብዛኛው የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት በኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒንግ (በቴክኖሎጂ) የተሳሰሩ በመሆናቸው፤ ደንበኞች በመረጡት የአገልግሎት መስጫ ማዕከል በአካል በመሄድ የፍጆታ ሂሳባቸውን መክፈል የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡