የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት አጀማመር በኢትዮጵያ

 

የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት ላይ መዋል የጀመረው በአጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት በ1890 ዓመተ ምህረት በጀርመን መንግስት በተገኘ በናፍጣ በሚሰራ ጄኔረተር አማካኝነት ነው፡፡ ከዚያን ወቅት ጀምሮ በሂደት ለምግብ ማብሰያም ሆነ ለብርሃን አግልግሎት ጥቅም ላይ ሲውል የነበረውን የማገዶና የጧፍ ተግባር በዘመናዊ የኤክትሪክ መሣሪያዎች እየተተካ ሄደ፡፡

የኤሌክትሪክ ብርሃን ማለት ምቾት ብቻ ሣይሆን ሁሉን ነገር መሆን መቻል መሆኑን በመገንዘብ ደረጃ በደረጃ በቤተ-መንግሰት ውስጥ ብቻ ተወስኖ የነበረው የኤሌክትሪክ ኃይል ከቤተ መንግስት መወጣት ጀመረ፡፡

በታሪክ ማስታወሻነቱ ግንዛቤ እንዲያስጨብጥ የኤሌክትሪክ ኃይል ከብርሃን እስከ ከፍተኛ የኢንዱስተሪ አንቀሳቃሽ የሆነበትን ኢትዮጵያዊ ዕድገቱን እንደሚከተለው እንቃኘው፡-

 • በ1890 ዓ.ም. የመጀመሪያ የናፍታ ጄኔሬተር አገር ውስጥ ገባ፡፡
 • በ1896 ዓ.ም. አጼ ሚኒልክ በምሰላቸው ገንዘብ ለማስቀረጽ 2ተኛ ጄኔሪተር ገዙ፡፡
 • በ1904 ዓ.ም. ጥይት ፋብሪካ ለማቆም 3ኛ ጄኔሬተር ተተከለ፡፡
 • በ1919 ዓ.ም. የአቡጀዲ ጨርቅ ፋብሪካ ለመትከል 4ኛ ጄኔሬተር ተገዛ፡፡
 • በ1920 ዓ.ም. አቅም ያላቸው የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የግል ጄኔሬተር በመግዛት መጠቀም ጀመሩ፡፡
 • በ1928 ዓ.ም. ጣሊያን ኢትዮጵያን በመውረሩ አዲስ አበባን ጨምሮ በተቆጣጠራቸው ከተሞች ውስጥ በዲዝል ኃይል መቅረብ ጀመረ፡፡

ለአብነት ያህል፡-

 • በ1929 ዓ.ም. በናዝሪት ፣ በድሪዳዋ እና በደሴ፣
 • በ1930 ዓ.ም በሐረር፣
 • በ1931 ዓ.ም. በጎንደርና በጅማ ከተሞች ጄኔሬተሮች ተተከልው አገልግሎት መስጠት መጀመራቸው ይታወሳል፡፡
 • ከዛ ቀጥሎ በ1928 ዓ.ም. መገባደጃ ላይ ኩኔል የተባለ የጣሊያን ኩባንያ ኤሌክትሪክ የማመንጨትና የመሸጥ ኃላፊነት ተሰጥቶት ነበር፡፡
 • በ1940 ዓ.ም. የሸዋ መብራት ኃይል የኤሌክትሪክ ሥራውን በኃላፊነት ተረከበ፡፡
 • በ1948 ዓ.ም በቻርተር የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ መብራትና ኃይል ባለስልጣን ተብሎ ሕጋዊ ሰውነት ይዞ ተቋቋመ፣
 • በ1952 ዓ.ም. ቆቃ ኃይል ማመንጫ ጣብያ ተገነባ፡
 • በ1956 ዓ.ም. ጢስ አባይ 1ኛ ኃይል ማመንጫ ተገነባ፡
 • በ1958 ዓ.ም. አዋሽ 2ኛ ተገነባ፣
 • በ1963 ዓ.ም. አዋሽ 3ኛ ተገነባ፣
 • በ1965 ዓ.ም. ፊንጫ ተገነባ፣
 • በ1980 ዓ.ም. መልካዋከና ተገነባ፣
 • በ1989 ዓ.ም. የኤትዩጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ተብሎ ተሰየመ፣
 • በ1993 ዓ.ም. ጢስ አባይ 2ኛ ተገነባ፣

በ1996 ዓ.ም ግልገል ጊቤ 1ኛ ተገነባ፣ በመቀጠል ግንባታውን ይበልጥ በማስፋት ተከዜ፣ ግልገል ጊቤ 2ኛ፣ ጣና በለስ፣ ፊንጫ አመርቲ ነሼ እና ጊቤ 3ተኛ የውኃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች እና እንዲሁም በንፋስ ኃይል የሚሰሩ ማመንጫ ጣቢያዎች እንደ አዳማ እና አሸጎዳ የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡

በአሁን ወቅት በአገሪቱ ያለውን የኃይል እጥረት በከፍተኛ ደረጃ ይቀርፋል ተብሎ የሚታሰበው የህዳሴ ግድብ በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡

የኤሌክትሪክ ኃይል ወደ አገራችን አገባቡ ዘግይቶ የመሆኑን ያህል ዕድገቱም እጅግ አዝጋሚ ሆኖ ቢቆይም፤ ሲጀመር መቀመጫውን ቤተ-መንግሰት ብቻ ተወስኖ የነበረውን የኤሌክትሪክ ኃይል በአሁን ወቅት በብርሃን ሰጨነቱ ብቻ ሳይሆን ለከተማውና ለገጠሩ ሕብረተሰብ የኑሮ ዕድገት መሠረት እንዲሁም ለአገር ብልጽግና ምሰሶ ሆኗል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የማቋቋሚያና ማሻሻያ ደንቦች

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ስራው እጅግ በመስፋቱ ለህብረተሰቡ አገልግሎት አሰጣጥ ምቹና ለደንበኛው በቅርበት ለማገልገል ታስቦ ከ2006 በጀት ዓመት ጀምሮ የኢትዮጰያ ኤሌክትሪክ አገልግሎትና የኢትዮጰያ ኤሌክትሪክ ኃይል በሚል ለሁለት ተከፈለ፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በዋናነት ኃይል ለደንበኞች የማሰራጨት ተግባርና ኃላፊነት ተሰጠው፡፡

አገልግሎቱ በሚኒሰትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈፃሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 691/2003 አንቀጽ 5 እና በመንግስት የልማት ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር 25/1984 አንቀጽ 47(1)(ሀ) መሠረት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ድርጀት ማቋቋሚያ ደንብ 303/2006 የኢትዮጰያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ድርጅት ሆኖ የተቋቋመ ሲሆን፤ ድርጅቱ በመንግስት የልማት ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር 25/1984 መሰረት ይተዳደራል፡፡

የኤሌክትሪክ ተደራሽነት

የኤሌክትሪክ ኃይል ለኢኮኖሚ ዕድገትና ለዘመናዊ አኗኗር መሰረታዊ በመሆኑ፤ ይህንን ወደ ገጠሩ ማህበረሰብ ተደራሽ ለማድረግ የአገር አቀፍ ኤሌክትሪክ አቅርቦት ፕሮግራም በ1998 ዓ.ም ተቋቁሟል፡፡  

የኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽነት GTP I

መንግስት በነደፈው መርሐግብር መሠረት ሁሉንም ህብረተሰብ የኤሌክክትሪክ ኃይል ተተቃሚ የማድረግ ፕሮግራም በGTP I (2003-2007 ዓ.ም) የኤሌከትሪክ ሽፋን ተደራሽነት 54.25 ከመቶ ደርሷል፡፡

የኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽነት GTP II

ምንም እንኳን የGTP II (2008-2012 ዓ.ም) እቅድ ዘመን ሊጠናቀቅ 16 ወራት የቀረው ቢሆንም በአሁን ወቅት ማለትም እሰከ መጋቢት 06 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ የተደረሰበት የኤሌክትሪክ ሽፋን 58.3444 ከመቶ ነው፡፡

Electric Access from 1983-2009 E.C

No

Performance of the utility

1983E.C

2009E.C

1

Numbers of electrified towns & villages

300

6,037

2

Coverage /access/ of Electric

8%

56%

3

Number of customers

400 thousand

Above 2.5 million

4

Length of installed medium & low voltage distribution lines in kms

9,972

201,504,00km

 • የአገር አቀፍ ኤሌክትሪክ አቅርቦት ፕሮግራም በ1998 ዓ.ም የተቋቋመበት ዋናው ምክንያት በመላው አገሪቱ ባሉት የገጠር ቀበሌዎችና መንደሮች የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል አቅርቦቱን መፍጠር ነው፡፡ እስካሁን ባለው የሥራ እንቅስቃሴ በርካታ የገጠር ቀበሌዎችና መንደሮች የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዲያገኙ የተደረገ ቢሆንም፤ ለወደፊት ከዚህ በላቀ ደረጃ ብዙዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ይጠበቃል፡፡
 • እስከ 1997 ዓ.ም ድረስ በሃገሪቱ 667 ከተሞችና መንደሮች ብቻ የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ የነበሩ ሲሆን፤ ፕሮግራም ቢሮው ከተቋቋመ በኋላ ከ1997 ዓ.ም አስከ የካቲት 30 ቀን 2011 ዓ.ም. ድረስ 6343 ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡
 • በአጠቃላይ በአሁኑ ወቅት 7010 የሚሆኑ ከተሞች፣ የገጠር ቀበሌዎችና መንደሮች የአሌሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ናቸው፡፡

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በአሁን ወቅት እየተወሰዱ ያሉ ስትራቴጂክ እርምጃዎች

 

ኤሌክትሪክ ለአገራችን ኢኮኖሚዊና ማህበራዊ የልማት እንቅስቃሴ የማይተካ ሚና ካላቸው የልማት ዘርፎች መካከል አንዱና ዋነኛው ነው፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎትም የተጣለበትን ይህን ታላቅ ሃገራዊ ሃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት የሚረዱ የተለያዩ ስትራቴጂክ እርምጃዎችን (Initiatives) በመቅረጽ ወደ ስራ ከገባ ሰነባብቷል፡፡ ተግባራዊ በመደረግ ላይ ካሉ ስትራቴጂክ እርምጃዎች መካከል ያልተማከለ አሰራር ስርዓት ትግበራ/Decentralization/፣ የስራ ሂደቶችን በቴክኖሎጂ መደገፍ /Process Automation & Technology/ እና ስራዎችን በሶተኛ ወገን አደራጅቶ ማሰራት/ Outsourcing/ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

 • አስቀድሞ በተቋሙ በመተግበር ላይ የነበረው አደረጃጀት በተለያዩ ምክንያቶች የማያሰራ ሆኖ በመገኘቱ በዚህ 2011 በጀት ዓመት ከሐምሌ 1 ቀን 2010 ዓ/ም ጀምሮ ያልተማከለ አሰራር ስርዓት ትግበራን /Decentralization/ ወደ ትግበራ እንዲገባ ተደርጓል፡፡ ተቋሙ በአሁን ወቅት የአገልግሎቱ አድማስ ይበልጥ ግልጽነትና ተጠያቂነትን ለማጠናከር በሚያመች፣ የክልሎችን አደረጃጀት በተከተለ ከክልል መንግስታት ጋር ትይዩ በሚያርጋቸው ባልተማከለ አደረጃጀት ማለትም በዘጠኝ ክልሎች እና በሁለት የከተማ አስተዳደር የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተደራጅቷል፡፡ እንዲሁም በ28 ዲስትሪክቶች እና በ546 የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት በማደራጀት አገልግሎቱን በማዳረስ ላይ ይገኛል፡፡
 • ይህ አገልግሎቱን ፍትሀዊና ተደራሽ ለማድረግ፣ ከግብዓት አቅርቦትና ከተገልጋዮች ቅሬታ ጋር በተያያዘ ያለውን እንግልት ለማስቀረት መሠረት በማድረግ የተከናወነ ነው፡፡
 • የስራ ሂደቶችን በአውቶሜሽን ቴክኖሎጂ መደገፍ /Process Authomation & Technology/ የተቋሙን ለውጥ ቀጣይነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ዘመኑ ያፈራቸውን ቴክኖሎጂዎችን በመተግበር ላይ የሚያተኩር የአሰራር ስረዓት ሲሆን፤ በዲስትሪብዩሽን ኔትወርክ አውቶሜሽን የስካዳና ስማርት ሜትሪንግ ቴክኖሎጂዎችን ተግባራዊ ለማድረግ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡
 • ቴክኖሎጂው የተቋሙን የፋይናንስ አሰራር፣ የሰው ሀብት አስተዳደር፣ የደንበኞች አገልግሎት፣ የጥሪ ማዕከልና የንብረት አስተዳደር ስራዎችን በሙሉ ወደ ዳታ ቤዝ ለማስገባትና ዘመናዊ፣ ግልፅና ቀልጣፋ አሰራር ስርዓት ለመፍጠር የሚያስችል የኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒግ /ERP/ የአውቶሜሽን ቴክኖሎጂ ፕሮጀክት ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል፡፡
 • የኢ.አር.ፒ. ፕሮጀክት አዲሱ የተቋሙን ያልተማከለ አደረጃጀትን ከመተግበሩ በፊት 83 በመቶ አፈጻጸም ደርሶ ነበር፡፡ ነገር ግን ተቋሙ አዲስ አደረጃጀትን በስራ ላይ በማዋሉ ዕቅዱ እንዲከለስ ተደርጓል፡፡ በተከለሰው የጊዜ ሰለዳ መሰረት የፕሮጀክት ትግበራ ስራው ከጥቅምት 2011 ዓ.ም ጀምሮ በሶስት ዋና ዋና ምዕራፎች ተከፋፍሎ ወደ ስራ እየተገባ ይገኛል፡፡ በዚሁ መሰረት ሲንትራላይዝድ የኢንተርኔት እና የተቋሙ የኢሜይል አግልግሎት ስራ ላይ እየዋለ ይገኛል፡፡ እንዲሁም በየካቲት 2011 ዓ.ም የኢንተርፕራይዝ ሪሶር ስፕሊኒንግ እና ተጓዳኝ የአይሲቲ መሰረተ ሌማት አቅርቦትና ትግበራ እና የSAP ዋና ዋና ሞጁሎች በአዲስ አባባ ሪጅን ተጀምሮ ወደ ለሎች ሪጅኖች በማስቀጠል ትግበራው 2011 በጀት ዓመት መጨረሻ ላይ ሙሉ በሙሉ እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል፡፡
 • ተቋሙ የሚሰጠውን አገልግሎት ለማሻሻል፣ ተደራሽነቱን ፍትሃዊ ለማድረግና በሃገሪቱ የሚስተዋለውን የስራ አጥነት ችግር ለመቅረፍ የሚያስችለው ስትራቴጂክ እርምጃ ደግሞ ስራዎችን በሶስተኛ ወገን አደራጅቶ ማሰራት /Outsourcing/ ሲሆን ተቋሙ በ2011 በጀት ዓመት የሚሰራቸውን የዲስትሪብዩሽን፣ ኮንስትራክሽን፣ ኦፕሬሽና ሜንቴናንስ ስራዎች በተቀላጠፈ እና ጥራቱን በጠበቀ መንገድ ለማከናወን እንዲችል ፍቃደኛ የሆኑ የውስጥ ሰራተኞች፣ በቀን ሰራተኝነት ተቀጥረው እየሰሩ ያሉና ሲሰሩ የነበሩ ግለሰቦች እና ከተቋሙ ውጭ የሚገኙ ኮንትራክተሮችን ጨምሮ በማደራጀት የተመረጡ ስራዎችን በሶስተኛ ወገን ለማሰራት የትኩረት አቅጣጫዎችን አስቀምጦ ወደ ስራ ገበቷል፡፡

በተጨማሪም፡-

 • በአዲስ አበባ ከተማ አሁን የሚታየውን የኤሌክትሪክ መቆራረጥ ለመቀነስና አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማቅረብ ከቻይና መንግስት በተገኘ 162.168 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ብድር የማሰራጫ መሰመሮች የማሻሻልና ዓቅም የማሳደግ ፕሮጀክት ስራ በመከናወን ላይ ሲሆን፤ የፕሮጀክቱ አጠቃላይ አፈጻጸም 78.6 በመቶ ደርሷል፡፡
 • እንዲሁም በስምንት ትላልቅ ከተሞች የዲሰትሪቡሽን መልሶ ግንባታና አቅም ማሳደግ ፕሮጀክት ስራ በመከናወን ላይ ሲሆን፤ ይህም ሁለት ዋና ዋና ፕሮጀክቶች ያቀፈ ነው፡፡ እነሱም፡- በዓለም ባንክ ፋይናንስ የሚሰራ በአዲስ አበባና ሰባት ዋና ዋና ከተሞች ዲስትሪቢዩሽን የመልሶ ግንባታና አቅም ማሳደግ ስራ አፈፃፀም 98.43 በመቶ የደረሰ ሲሆን፣ በOFID ፋይናንስ የሚሰራ በአዲስ አበባ ከተማ ዲስትሪቢዩሽን የመልሶ ግንባታና ማሻሻያ ፕሮጀክት ስራ 86.92 በመቶ ደርሰዋል፡፡ በአጠቃላይ ፕሮጀክቱ ከተጀመረ ጀምሮ የተደረሰበት አፈፃፀም 94.99 ከመቶ ነው፡፡

የወደፊት ዕቅድ፡-

 • በአሁኑ ወቅት በዓለም ባንክ ጥናት መሰረት በሃገራችን የሚገኘውን የህብረተሰብ ክፍል ሙሉ በሙሉ የሃይል ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችል ‘’ብርሃን ለሁሉ’’ ጥናት ተጠንቶ የትግበራ ምዕራፍ የተጀመረ ሲሆን፤ በቀረበው ጥናት መሰረት በ2025 ዓ.ም የሃገሪቱን 65 ከመቶ የሚሆነውን ህዝብ በቀጥታ ከግሪድ ሃይል በማገናኘት እና ቀሪ 35 በመቶ የሚሆነውን በተለያዩ የሃይል አማራጮች /በኦፍ ግሪድ ሃይል/ በማቅረብ የኤሌክትሪክ ተጠቃሚነትን መቶ ፐርሰንት ሽፋን ለማድረስ ታቅዶ እየተሰራ ይገኛል፡፡