የአዲስ አበባ ከተማን በፍጥነት ማደግን ተከትሎ የህብረተሰቡ የኃይል ፍላጎት ከመቼዉም ጊዜ በበለጠ እየጨመረ መጥቷል፡፡ እያደገ የመጣውን የሃይል ፍላጎት መሸከም የሚችል የኤሌክትሪክ ማሰራጫ መስመር አብሮ ያላደገ በመሆኑ ለተደጋጋሚ የኃይል መቆራረጥና መዋዥቅ እንዲሁም የኃይል ብክነት ሲያጋልጥ ይስተዋላል፡፡ይህም በከተማዋ ኤሌክትሪክ ተጠቃሚ የህብረተሰብ ክፍል እና በተቋሙ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ያሳድራል፡፡ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የኤሌክትሪክ ማሰራጫ መስመር መልሶ ግንባታና አቅም ማሳደግ ፕሮጀክት ቀርፆ ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ የአዲስ አበባ ዲስትሪቢዩሽን መልሶ ግንባታና አቅም ማሳደግ ፕሮጀክት ተቀርፆ በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡powerchaina10