header bgLattest

ዘመናዊ የክፍያ ስርዓት ለመተግበር ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ነው

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዘመናዊ የከፍያ ስርዓት ተግባራዊ ለማድረግ የቅድመ ዝግጅት ስራ በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ ደንበኞች የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳባቸው በዘመናዊ መንገድ ለመፈፀም የሚያስችላቸው አሰራር ተግባራዊ የሚደረገው ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በመተባበር ነው፡፡

የዘመናዊ ክፍያ ስርዓቱ ተጠቃሚ የሚሆኑት የከፍተኛ ኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚዎች ማለትም ሁሉም የኢንዱስትሪ ደንበኞች፣ የግል ድርጅቶች፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ሲሆኑ፤ በተጨማሪም ማንኛውም ፍቃደኛ የሚሆኑ የዝቅተኛ ኃይል ተጠቃሚ ደንበኞችም በአሰራሩ ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ፡፡

አሰራሩ ለደንበኞችና ለተቋሙ ከሚያስገኛቸው ጠቀሜታዎች በዋናነት ወደ ዘመናዊ አሰራር የሚያስገባ በመሆኑ፣ የደንበኞች መረጃ በባንኩና በተቋሙ በጥንቃቄ ይያዛል፡፡ ቀልጣፋና ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችልና ደንበኞች ወርሀዊ ፍጆታን ለመክፈል ከሚያቃጥሉት ጊዜም ይታደጋል፡፡ አሰራሩ ግልፅና በደረሰኝ የሚከናወን በመሆኑ፤ለክትትልና ለቁጥጥረም በጣም ያመቻል፡፡

የ905 ነፃ የጥሪ ማዕከልና ተደራሽነቱ

 የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የአገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመንና የተቋሙን መረጃዎች ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ በርካታ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡

መረጃ ተደራሽ ከሚደረግባቸውና ተቋሙና ደንበኞቹ ከሚያገናኙ መንገዶች አንዱ የ905 ነፃ ጥሪ ማዕከል ይጠቀሳል፡፡

DSC 1109

የ905 ነፃ የጥሪ ማዕከል ደንበኞች የተለያዩ ቅሬታዎች፣ጥቆማዎች እንዲሁም የሃይል መቆራረጥና መዋዥቅ ሲያጋጥማቸው በቀላሉ እንዲያሳውቁ ለማስቻል ሲባል በዘመናዊ መልክ በ2007 ዓ.ም ነው የተቋቋመው፡፡

ማዕከሉ ሲጀምር 30 መቀመጫዎች የነበሩት ሲሆን፤ በሂደት በተደረገለት ማስፋፊያ 50 መቀመጫዎች እንዲኖሩት ተደርጓል፡፡

የጥሪ ማዕከሉ የሚተዳደረው በተቋሙ ነው፡፡ ሆኖም ኢትዮ ቴሌኮም የኔትዎርክ ግንኙነት፣ ግንኙነቱን ለማድረግ የሚያስፈልጉ ዕቃዎችና የመስሪያ ቦታው ያቀርብለታል፡፡

537 ሺህ ደንበኞች የቅድመ ክፍያ ቆጣሪ አገልግሎት ተጠቃሚ ሆኑ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት 537 ሺህ ደንበኞችን የቅድመ ክፍያ ቆጣሪ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ አደረገ፡፡ የቅድመ ክፍያ አገልግሎቱ በሁለቱ ከተማ አስተዳድሮች (አዲስ አበባና ድሬዳዋ) እና በሰባት ክልሎች ተግባራዊ በመደረግ ላይ ነው፡፡

prep

ሲስተሙ የተጀመረው በ1999 ዓ.ም ሲሆን፤ በአሁን ወቅት በአዲስ አበባ፣ በድሬዳዋ፣ በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በደቡብ፣ በትግራይ፣ በሶማሊያ፣ በአፋርና በሐረር በሚገኙ በ67 የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት እየተሰጠ ይገኛል፡፡

ከ537 ሺህ የቅድመ ክፍያ ተጠቃሚዎች መካከል 370 ሺህ ደንበኞች አዲስ አበባ የሚገኙ ናቸው፡፡ 41 የአገልግሎት መስጫ ማዕከላትም በከተማው አገልግሎቱን ይሰጣሉ፡፡

ሴቶችን ወደ ኃላፊነት ለማምጣት ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባ ተገለፀ

Mr 8

አለም አቀፍ የሴቶች ቀን (ማርች 8) በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ108 እንዲሁም በሀገራችን ለ43ኛ ጊዜ “የላቀ ትኩረትና ቁርጠኝነት ለሴቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት” በሚል መሪ ቃል የካቲት 29 ቀን 2011 ዓ.ም ተከብሯል፡፡

በበዓሉ የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች፣ ሰራተኞችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

ብልሹ አሰራሮችን አይደግፉ፤ ይከላከሉ!

የመልካም ሰራተኞቻችንን ስምና ምግባር የሚያበላሹ ስነ ምግባር የጎደላቸው ሰራተኞች ሲያጋጥምዎ ተባባሪ ከመሆን ይቆጠቡ!

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለደንበኝነት የሚያበቃዎን መስፈርት አሟልተው አገልግሎታችንን ሲፈልጉ ተገቢውንና ከእርስዎ የሚጠበቀውን መልካም ስነ ምግባር ብቻ ይከተሉ!

Um

ጊዜን ለመቆጠብ፣ የኤሌክትሪክ አገልግሎቱን በፍጥነት ለማግኘት ሲሉ ስነ ምግባር የጎደላቸውን ሠራተኞች መልካም ያልሆነ ተግባር አይደግፉ፤ ተቋሙ ያለበትን ጫና ይረዱ! ጉቦ አይስጡ! በአግባቡ ይስተናገዱ!

Search