የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የደንበኞችንና የውስጥ አሰራሩን ቀልጣፋና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ ለማድረግ የአውቶሜሽን እና የመረጃ አያያዝ ስርአት ትግበራ ዛሬ ሚያዝያ 22 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ይፋ አድርጓል፡፡

Image may contain: 6 people, people smiling, beard

የትግበራ ስርአቱ የመጀመሪያ ምዕራፍ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚገኙ አንድ ሚሊየን ደንበኞችን በአዲሱ ሲስተም እንዲገለገሉ ያስችላል፡፡

ፕሮጀክቱ የደንበኞች ግንኙነት አስተዳደር፣ የቢል ሲስተም፣ የቆጣሪ መረጃ አስተዳደርና የኢነርጂ መረጃ አስተዳደር አገልግሎት አሠጣጥን በከፍተኛ ሁኔታ ያዘምናል፡፡

የተቋሙ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሽፈራው ተሊላ የኢ.አርፒ. ፕሮጀክት ተቋሙ በቴክኖሎጂ የተደገፈ፣ የተቀላጠፈና ዘመናዊ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማስቻልና የደንበኞችን ዕርካታ በማሻሻል የተቋሙን ገቢ ለማሳደግ ትልቅ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ብለዋል፡፡

Image may contain: 3 people, people sitting, table and indoor

ዋና ስራ አስፈፃሚው ቴክኖሎጂው ሰራተኛው ይበልጥ ውጤታማ ተግባራትን እንዲያከናውኑ የሚያደርግና አገልግሎቱን ለማዘመን ስለሚያግዝ ሁሉም ሠራተኞች በአግባቡ ሊተገብሩት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

Image may contain: 10 people, people sitting

በስነ-ስርዓቱ ላይ የህበረተሰቡን የሀይል ፍላጎት ለማርካት እንዲያችል መሰል የዘመናዊ ቴክኖሎጂ ግብዓቶችን ተግባራዊ ማድረግ የሚያበረክተው አስተዋፅኦ የላቀ በመሆኑ በቀጣይ መሰል ፕሮጀክቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተገልጿል፡፡

ፕሮጀክቱ በህንድ ማሂንድራ ካምፓኒ አማካኝነት የተተገበረ ሲሆን፣ በቀጣይ በአገር አቀፍ ደረጃ በግንቦት መጨረሻ ተግባራዊ መደረግ የሚጀምር ይሆናልም ተብሏል፡፡