የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከፍተኛ አመራሮች በተቋሙ የ2011 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀምና የ2012 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ለሶስት ተከታታይ ቀናት ውይይት አካሄዱ፡፡ ውይይቱ የተካሄደው ከሐምሌ 19 -21 ቀን 2011 ዓ.ም በቢሾፍቱ ከተማ ነው፡፡67558913 2653654177980012 4711984173487751168 n

በውይይት ግምገማው የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሽፈራው ተሊላ ጨምሮ የክልልና የከተማ አስተዳደር ኤሌክትሪክ አገልግሎት ስራ አስፈፃሚዎች እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡

አመራሩ በበጀት ዓመቱ የተከናወኑ ዋና ዋና ሥራዎችን፣ ያጋጠሙ ችግሮችና የተወሰዱ የመፍትሄ አቅጣጫዎች በጥልቀት የገመገመ ሲሆን፤ የኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላንኒግና የስምንቱ ከተሞች መልሶ ግንባታ ፕሮጀክት አፈፃፀሞች፣ የተቋሙን ገፅታ ለመገንባት የሚደረገው ጥረት አበረታች መሆኑ ተመልክቷል፡፡
የተቋሙ የኦዲት ሪፖርት በመዘጋጀት ላይ መሆኑና አደረጃጀት ለማሻሻል የሚደረገውንም ጥረት በጠንካራ ጎን ገምግሟል፡፡

ቀልጣፋና ጥራት ያለው አገልግሎት አለመስጠት፣ ተቋሙ ከሚያገኘው ገቢ የማይተናነስ ወጪ መኖሩ፣ የኃይል ስርቆትን አለመከላከል፣ የመረጃ አያያዝ ችግር፣ የመልካም አስተዳደርና የስነ ምግባር ችግሮች መታየታቸውን በድክመት የሚታዩ መሆኑን አስቀምጧል፡፡

የግብዓት አቅርቦት ውስንነት፣ የተጠያቂነት ስርዓት አለመጎልበት፣ የገቢ አሰባሰብ አናሳ መሆን፣ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ አለማጠናቀቅ፣ አዲስ ኃይል ፈላጊ ደንበኞች በቶሎ አለማስተናገድና የአገልግሎት ጊዜያቸው ያለፈባቸው ንብረቶች ለማስወገድ የተጀመረውን ስራ አናሳ መሆን በተቋሙ የታዩ ሌሎች ድክመቶች መሆናቸውን ተጠቅሷል፡፡

ይህንንም በቀጣይ በጀት ዓመት ለማስተካከል የቅድመ ጥገናና መልሶ ግንባታ ስራ በወቅቱ ማከናወን፣ በማሰራጫ መስመሮች ላይ የሚደረገውን ክትትልና ቁጥጥር ማጠናከር፣ ቀልጣፋና ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት፣ የኃይል ስርቆትን መከላከል፣ የተጠያቂነት ስርዓትን ማጎልበት፣ ስራዎች በኃላፊነት ስሜት እንዲሰሩ ተገቢ የሆነ ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ፣ የኦዲት ግኝቶችን ማስተካከል፣ ያገለገሉ ንብረቶችን በጨረታ ማስወገድ፣ ጠንካራ የኢንስፔክሽን ስራ መስራትና የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብን በቁርጠኝነት መሰብሰብ አስፈላጊ መሆኑን ከፍተኛ አመራሩ ገምግሟል፡፡

አመራሩ በቀጣይ በጀት ዓመት እነዚህንና ሌሎች መሰረታዊ ሥራዎችን በማከናወን የተቋሙን አገልግሎት ማሻሻል እንደሚገባ በሰፊው ተወያይቷል፡፡

በመጨረሻም አመራሩ በወጪ ቅነሳ፣ በቅድመ ጥገና መልሶ ግንባታ ሥራዎች፣ በገቢ አሰባሰብ፣ በኢንስፔክሽን ስራ፣ በዘመናዊ አውቶሜሽን ቴክኖሎጂ ትግበራ፣ በተጠያቂነት ስርዓትና በኃይል ስርቆት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት እንዳለበት አቅጣጫ አስቀምጧል::