ተቋሙ አንድ ሚሊዮን አዲስ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ ነው

በ2011 በጀት ዓመት በተቋም ደረጃ 657,694 ደንበኞች የኤሌክትሪክ ኃይል ለማገናኘት ታቅዶ 195,264 ደንበኞች ማገናኘት የተቻለ ሲሆን፣ በበጀት ዓመቱ የግብዓት ማነስ፣ የፋናንስ ዕጥረት የትራንስፎርመሮች መቃጠልና መዘረፍ እንዲሁም ከአቅም በላይ መጫንና የመሳሰሉት ተግዳሮቶች የአፈፃፀም ውጤቱን ዝቅ እንዲል ምክንያት የሆኑ እንቅፋቶች ነበሩ፡፡721A6894

በ2011 በጀት ዓመት እንደዚሁ የኤሌክትሪክ አቅርቦት ተደራሽነት ለማሳደግ በዕቅድ ከተያዙ 382 አዳዲስ ከተሞች ውስጥ 213 ከተሞች ኤሌክትሪክ አንዲያገኙ ተደርጓል፡፡ በመልሶ ግንባታ ስራ ደግሞ 23 ከተሞችን ለማከናወን ታቅዶ፤ 16 ከተሞችን በማገናኘት የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ ተችሏል፡፡

በአጠቃላይ ተቋሙ በበጀት አመቱ 405 ከተሞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ አቅዶ፣229 ያህሉን በማከናወን የዕቅዱን 56.54 በመቶ ማሳካት ችሏል፡፡    

በ2012 በጀት አመት አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት ለማሳደግ የመልሶ ግንባታና የአቅም ማሳደግ ስራዎች በመስራት የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን ለማሳደግ ይሰራል፡፡ ከዋናው ግሪድ በተጨማሪ አማራጭ የኃይል ምንጮችን በመጠቀም የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን ለማስፋት የሚሰራ ይሆናል፡፡

የአዲስ ደንበኞችን ቁጥር ማሳደግ፣ የኤሌክትሪክ አገልግሎት አስተማማኝነትን ማሻሻል፣ የተገልጋይ እርካታንና የደንበኞችን ቁጥር ማሳደግ፣ የኤሌክትሪክ አገልግሎቱን ባላገኙ ቦታዎች የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማትን ማዳረስ፣ የኤሌክትሪክ ብክነትን መቀነስና የተቋሙን ገቢ ማሳደግ የ2012 በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎች ናቸው፡፡86954

በዚህም በበጀት ዓመቱ በአገር አቀፍ ኤሌክትሪክ አቅርቦት ፕሮግራም 150,000 ደንበኞች፣ በክልሎች በመደበኛ በጀት መርሐግብር 765,000 ደንበኞች፣ በ6ቱ ከተሞች የመልሶ ግንባታና አቅም ማሳደግ ፕሮጀክት 65,000፤ በሶላር ፓናል ለገጠር መኖሪያ ቤቶች 20,000 በአጠቃላይ አንድ ሚሊዮን ደንበኞች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል፡፡


Print