የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዛሬ ጥር 23/2012 ዓ.ም የኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒንግ ፕሮጀክት ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት በድምቀት አስመረቋል፡፡ERPPIC1

በምረቃ ስነ-ስርዓቱ የትምህርት ሚኒስቴር ሚንስትርና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር)፣ በውሀ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ዘርፍ ሚንስትር ዴኤታ ዶ/ር ፍሬህይወት ወልደሃና፣ የቴክ ማህንዲራ ፕሮጀክት ምክትል ፕሬዘዳንት ፕራስድ ኮትኪላ፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሺፈራው ተሊላን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የተቋሙ ማኔጅመንት አባላት ተገኝተዋል፡፡

በሰነ-ስርዓቱ የትምህርት ሚኒስቴር ሚንስትርና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር) መልዕክት ያስተላለፋ ሲሆን ተቋሙ የኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒንግ የአሰራር ስርዓትን ተግባራዊ ማድረጉ ከአገልግሎት አሰጣጡ ጋር የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ከፍተኛ አስተዋጾ ይኖረዋል ብለዋል፡፡ERPPIC2
ሚኒስትሩ አክለውም የአሰራር ስርዓቱ ስማርት ሜትርና የእስካዳ ሲስተምን ያካተተ መሆኑ ደግሞ ከሃይል ብክነትንና ስርቆትን ጋር የተያያዙ ችግሮችን ለመፍታት ጉልህ ሚና ኖረዋል ብለዋል፡፡
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ምክትል ስራ አስፈጻሚና የአውቶሜሽንና ኢነርጂ ማኔጅመንት ስራ አስፍጻሚ አቶ ደመቀ ሮቢ በአደረጉት ንግግር ተቋሙ ተግባራዊ ያደረገው የኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒንግ የአሰራር ስርዓት አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀና ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችልና የተቋሙን አደረጃጀትና የስራ ፍሰት ለማስተካከል እንዲሁም የቴክኒክ ልህቀትን እውን ለማድረግ የሚያግዝ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

አቶ ደመቀ አክለውም የፕሮጀክቱ መተግበር የተቋሙን የፋይናንስ አቅም፣ የሀይል አቅርቦትን እና በአጠቃላይ የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል ቁልፍ ሚና እንደሚኖረው ገልፀዋል፡፡

የፕሮጀክቱ የገንዘብ ምንጭ የአለም ባንክ ሲሆን የፕሮጀክቱን ስምምነት ወስዶ ያከናወነው ደግሞ ቴክ ማህንዲራ የተሰኘው የህንድ ኩባንያ ነው፡፡
የፕሮጀክቱ ጠቅላላ ወጭ 58.90 ሚሌዮን የአሜሪካን ዶላር ሲሆን 46.04 ሚሊዮን ዶላሩ ለትግበራና ስታንዳርድ ዋራንቲ፣ 12.86 ሚሊዮን ዶላሩ ደግሞ ለላይሰንስና ለሜይንተናነስ ሳፖርት ስራ የሚከፍል የአገልግሎት ክፍያ ነው፡፡

የኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒንግ ፕሮጀክት ትግበራ በአራት ምዕራፍ በሁለት ዋና ዋና የስራ ክፍሎች ተከፍሎ ተግባራዊ የተደረገ ሲሆን ኢንፍራስትራክቸርና ሁለተኛው ደግሞ አፕሌኬሽን ነው፡፡
ተቋሙ ተግባራዊ ያደረገው የኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒንግ የአሰራር ስርዓት 17 የአፕሌኬሽን ሞጁሎች ያሉት ሲሆን የፋይናንስና ኮንትሮል፣ የሰው ሀብትና ፔሮል፣ የመረጃ ማዕከል፣ የንብረት አስተዳደርና የእቃ ግምጃ ቤት፣ የኢንተርፕራይዝ አሴት አስተዳደር፣ የጥሪ ማዕከል፣ የፕሮጀክት አስተዳደር እና የጥራት አስተዳደር፣ የንባብና የቢል እንዲሁም ከገንዘብ ስብሰባ ጋር የተገናኙ ሞጁሎች በሁሉም የተቋሙ ከልሎችና የስራ ክፍሎች ተግባራዊ ተደርገዋል፡፡

ፕሮጀክቱን ውጤታማ እንዲሆን ከፕሮጀክቱ ጋር የተገናኙ የአቅም ማጎልበቻና የቴክኖሎጂ ሽግግር ስልጠናዎች የተሰጡ ሲሆን ከነዚህም መካከል የኮር ፣ የሻምፒዮንና የሲሰተም ተጠቃሚ ክፍሎች የቴክኒክ እና የሲሰተም አጠቃቀም ስልጠና እዲወስዱ ተደርገጓል፡፡

በዕለቱ ተቋሙ ያሰራውን አዲስ መለያ አርማ( ሎጎ) ያስመረቀ ሲሆን በመጨረሻም ለፕሮጀክቱ መሳካት አስተዋጽዖ ላበረከቱ ተቋማት፣ ባለ ድርሻ ካላት፣ የስራ ክልሎችና የተቋሙ ሰራተኞች የእውቅና ሽልማት ከተበረከተላቸው በኋላ ስነ-ስርዓቱ ተጠናቋል፡፡