ሃዋሳ ከተማ የመልሶ ግንባታ ፕሮጀክት አፈፃፀም 98% ደረሰ

48221834 2275258942486206 7347437885122936832 n

በሃገራችን በሚገኙ ስምንት ትላልቅ ከተሞች የኤሌክትሪክ ሥርጭት መስመሮች የማሻሻልና ዓቅማቸውን የማሳደግ ሥራ እየተሰራ መሆኑ ይታወሳል፡፡ ሥራው በዚህ በጀት ዓመት ለማጠናቀቅ ሰፊ ርብርብ እየተደረገ ሲሆን በስምንቱም ከተሞች አጠቃላይ የፕሮጀክቱ አፈፃፀም ከ90 ፕርሰንት በላይ ደርሷል፡፡

ግንባታው ከሚከናወንባቸው ከተሞች አንዱ በሆነው የሃዋሳ ከተማ እስካሁን፣
• 48.8 ኪ.ሜ የሚሸፍን 1200 አዳዲሰ የመካከለኛ መስመር የኮንክሪት ምሰሶዎች ተተክለዋል፣
• 47.5 ኪሜ የሚሸፍን 1283 አዳዲስ የዝቅተኛ መስመር የኮንክሪት ምሰሶዎች ተተክለዋል፣
• 24 ነባር የሥርጭት ትራንስፎርመሮች የማሻሻል ሥራ የተከናወነ ሲሆን፤ 11 አዳዲስ ትራንስፎርመሮችም ተተክለዋል፣
• ፕሮጀክቱ በከተማው ለ3914 ደንበኞች ተጠቃሚ ያደርጋል፣
• 489 አዳዲስ የመንገድ መብራቶችም ተተክለዋል፡፡
• እንዲሁም በአሁን ወቅት ነባሩን የዝቅተኛ ቮልቴጅ መስመሮች ሙሉ ለሙሉ በማፈረስ በአዲሱ ተተክተው አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል፡፡ 
• ፕሮጀክቱ 7 የመካከለኛ መስመር መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች (switching stations) የተገነባለት ሲሆን፤ እነዚህ ጣቢያዎች ለመቆጣጠር የሚያስችል አንድ የቴክኖሎጂ ማዕከል (scada system) ተሰርቶለታል፡፡ ይህም የኤሌክትሪክ ሥርጭቱ አሰራር ለማዘመን ጠቀሜታው እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡

በከተማው አብዛኛው የፕሮጀክቱ ግንባታ ሥራ ተጠናቆ፤ አፈፃፀሙም 98 ፐርሰንት ደርሷል፡፡ ቀሪ ሥራው ሲጠናቀቅ በከተማው እየተስተዋለ የሚገኘውን የሃይል መቆራረጥና መዋዥቅ በከፍተኛ ደረጃ የሚቀንሰው ይሆናል፡፡ ከዚህ ቀደም ከነበረው በላቀ መልኩ የሃይል አቅርቦቱ ያሻሽለዋል፡፡ የተገነባውም በአስተማማኝ ኬብልና በኮንክሪት ምሰሶ በመሆኑ፤ አደጋ የመቋቋምና የመከላከሉ ሁኔታ በጣም ከፍተኛ ነው፡፡

እነዚህ መሰረተ ልማቶች የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጡ ሲባል በብዙ ገንዘብ የሚገነቡ በመሆናቸው፤ ህብረተሰቡ ሁልጊዜ እንደራሱ ንብረት ሊጠብቃቸው ይገባል፡፡

47687098 2275259179152849 8556794023048642560 n


Print