የኢትዮ-ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብ የሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀሙን ገመገመ፡፡

 

spoከተመሠረተ 58 ዓመት ያስቆጠረው የኢትዮ-ኤሌክትሪክ ክለብ የቀድሞው አንጋፋ ስሙን ለመመለስ ጠንክሮ እየስራ እንደሆነ ታህሳስ 02 ቀን ባካሄደው የ2011 የሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ አስታውቋል፡፡
በዕለቱም የክለቡ ስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ኢሳያስ ደንድር በተገኙበት የኢትዮ-ኤሌክትሪክ ስፖርት በተለያየ ዘርፍ ከያዛቸው ሰፖርተኞችና ባለድርሻ አካላት ጋር ክለቡ አሁን ባለለበት ደረጃና በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ተወያይቷል፡፡


በውይይቱም ወቅት ለልምምድና ለውድድር የሚያስፈልጉ ግብዓቶች መሟላታቸውን፤ ከተለያዩ ኩባንያዎች ድጋፍ እንዲገኝ መደረጉን፤ የሥራ አመራር ቦርዱ በክለቡ የውጪ ዜጋ ተጨዋቾች እንዳይካተቱ መወሰኑንና ለታዳጊዎች ዕድል መሰጠት እንዳለበት ተወስኗል፡፡
በተያያዘም የክለቡን ህልውና በአስተማማኝ መሠረት ላይ ለመጣል የክለቡን ገቢ ማሣደግና ወጪን መቀነስ፤ ከአሰራርና አደረጃጀት ጋር በተያያዘ የታዩ ችግሮችን መፍታት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራል ብለዋል፡፡
አዲሱ የስራ አመራር ቦርድ የቡድኑን የቀድሞ አንጋፋ ስምና ዝና ለመመለስ የአጭር፣ የመካከለኛና የረዥም ጊዜ ዕቅዶችን አውጥቶ እየሰራ እንደሆነ በሪፖርቱ ተጠቅሷል፡፡

48366461 2278607108818056 1432682145121304576 n


Print