የሻሸመኔ የእንጨት ምሰሶ ማምረቻ ማዕከል በቀን 200 ምሰሶዎችን የመንከር አቅም አለው


48358141 2279046622107438 7826809638979895296 nየኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኤሌክትሪክ ሃይል ለተጠቃሚዎች ለማሰራጭት ግብዓት የሆነውን የእንጨት ምሰሶ የሚያመርትባቸው አራት ማዕከላት አሉት፡፡ አዲስ አበባ፣ ሻሸመኔ፣ ባህር ዳርና ነቀምቴ ላይ ይገኛሉ፡፡

ከእነዚህ ማዕከላት አንዱ የሆነው የሻሸመኔ የእንጨት ምሰሶ ማምረቻ ማዕከል፣
• የተቋቋመው በ2000 ዓ.ም ነው፣
• በቀን በመደበኛ የሥራ ሰዓት በአማካኝ 200 የእንጨት ምሰሶዎችን ይነክራል፣
• በ3 ሰዓታት ከ80 – 100 ምሰሶዎችን መንከር የሚያስችል ዓቅም አለው፡፡ ጥሬ እንጨቱን ለማዘጋጀት የሚወስደው ግዜ ሳይጨምር፣
• አምስት አይነት የእንጨት ምሰሶዎችን የመንከር አቅም ያለው ሲሆን፤ ባለ 8፣ 9፣ 10፣ 11 እና 12 ሜትር ቁመት ያላቸው ናቸው፣ 
• ምሰሶዎቹ ለዝቅተኛና ለከፍተኛ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ያገለግላሉ፣
• ማዕከሉ በኢትዮጰያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ስር ለሚገኙ ለሁሉም የአገልግሎት መሰጫ ማዕከላት ምርቱን ያከፋፍላል፣
• በዓመት በአማካኝ 40 ሺ ምሰሶዎችን ይነክራል፣
• ለግብዓትነት የሚሆነው ደን ባህር ዛፍ ሲሆን፤ ጥሬ ምርቱን የሚያቀርቡ አቅራቢዎች አሉ፡፡ ይህም ለሌሎች የሥራ ዕድል እንዲፈጠር አስችሏል፣

*** ምሰሶ መንከር ማለት ለሃይል ማሰራጫነት የሚያገለግል የእንጨት ምስሶን ለረጅም ጊዜ አገልግሎት እንዲሰጥ በኬሚካል ማከም ሲሆን፤ ኬሚካሉ በውጭ ምንዛሬ ከውጭ ሃገር የሚገዛ ነው፡፡ ከፍተኛ ገንዘብ የሚጠይቅ መሆኑን ማስተዋል ይቻላል፡፡

48226629 2279044818774285 8823657237550465024 n


Print