ለኢንዱስትሪዎች መስፋፋት የኤሌክትሪክ አገልግሎት ሚና ከፍተኛ ነው

48270247 2280557985289635 3571542052841717760 n

ኤሌክትሪክ ለአንድ ሃገር ሁለተናዊ ዕድገት መሰረት ነው፡፡ በሃገራችንም ከእያንዳንዱ የልማት ሥራዎች በስተጀርባ የኤሌክትሪክ አገልግሎት አለ፡፡

በተለይ ሃገሪቱ ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ ለመሸጋገር በምታደረገው ሰፊ ርብርብ የዚህ ዘርፍ ሚና እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡ እንዲሁም በአሁን ወቅት በሃገር አቀፍ ደረጃ ከሚገነቡ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ዋነኛው አንቀሳቃሽ ሞተር ኤሌክትሪክ መሆኑን ማስተዋል ይቻላል፡፡

ከነዚህም ፓርኮች ውስጥ የሃዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ አንዱና ለዚህ ትልቅ ማሳያ ይሆናል፡፡ ታህሳስ 23 ቀን 2009 ዓ.ም ሥራ የጀመረው ኢንዱስትሪ ፓርኩ፤ በመጀመሪያ ምዕራፍ 52 የሚሆኑ ሼዶች ተገንብቶለት ሁሉም በባለሃብቶች የተያዙ ሲሆን 20 የጨርቃ ጨርቅ አምራች ኢንዱስትሪዎች ምርት ማምረትና ወደ ውጭ መላክ ጀምረዋል፡፡ ለ22 ሺ ሰዎች የስራ ዕድልም ፈጥሯል፡፡ በተጨማሪም የተለያዩ ሃገር በቀል ማህበራትና ድርጅቶች በጥበቃ፣ በምግብ አቅርቦት፣ በጽዳትና መሰል የስራ ዘርፎች እንዲሳተፉ ዕድል ከፍቷል፡፡

ተቋማችንም ለፓርኩ ውጤታማነት አስተማማኝና ያልተቆራረጠ የኤሌክትሪክ ኃይል እያቀረበለት ይገኛል፡፡ አሁን ከ12 እስከ 15 ሜዋ የሚደርስ ኃይል እየተጠቀመ ሲሆን በሙሉ አቅሙ ወደ ሥራ ሲገባ፤ 200 ሜዋ የኤሌክትሪክ ኃይል ያስፈልገዋል፡፡ እንዲሁም ለ60 ሺ ሰዎች የስራ ዕድል ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ከእያንዳንዱ የሃገሪቱ ልማት ስኬት ጀርባ የኤሌክትሪክ አገልግሎት አለ፡፡

48226655 2280567285288705 6106771684717494272 n


Print