ተቋሙ ትራንስፎርመሮችን ለመግዛት ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ የሚበልጥ የግዥ ውል ስምምነት ተፈራረመ

48406954 2291333997545367 3604788565751365632 n

 

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልገሎት 17 ዓይነት ትራንስፎርመሮች ለመግዛት ሰባት የሀገር ውስጥ አምራች ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ ለይቶ ከሁለቱ ድርጅቶች ጋር በትላንትናው ዕለት የግዥ ውል ስምምነት ተፈራርሟል፡፡ ቀሪዎች አምስት አቅራቢ ድርጅቶችም በቀጣይ ቀናት ስምምነቱ የሚፈፅሙ ይሆናል፡፡

ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ ሽፈራው ተሊላ በስምምነቱ ወቅት እንደገለፁት በየጊዜው የህበረተሰቡ የኤሌክትሪክ ኃይል ፍላጎት እየጨመረ በመምጣቱና ለደንበኞች የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት፤ ስምምነቱ ትልቅ ጠቀሜታ አለው ብለዋል፡፡ አክለውም የግዥ ስምምነቱ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማግኘት ለረዥም ጊዜ ከፍለው እየተጠባበቁ የሚገኙ ደንበኞች ጥያቄ ለመመለስ እንደሚያስችል ገልፀዋል፡፡ የደንበኞችን ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ለማሳደግ እየተሰሩ ላሉ ስራዎቸም ትልቅ ግብአት እንደሆነ ነው የጠቆሙት፡፡

ስምምነቱ የፈፀሙት ሁለት ተቋማት አባይ ትርንፎርመሮች አምራች ኃ.የተ.የግ.ማ እና አዶርን ትርንፎርመሮች አምራች ኃ.የተ.የግ.ማ የተሰኙ ሲሆኑ፤ ጥራት ያላቸው ትራንስፎርመሮች በውሉ በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት አምርቶ ለማቅረብ ርብርብ እንደሚያደርጉ በተወካዮቻቸው አማካኝነት ገልፀዋል፡፡ ተቋሙም ከዚህ በፊት ይጠቀምበት የነበረው የግዥ አሰራር በመቀየር በቀጥታ እንዲያቀርቡ ዕድል ስላመቻቸላቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ስምምነቱ በሁለት ምዕራፎች የሚፈፀምና ለአንድ አመት የሚቆይ ሲሆን፤ ከ50 አስከ 1250 ኪሎ ቮልት አምፒር አቅም ያላቸው 4,978 ትራንሰፎርመሮች ያካትታል፡፡ ይህም በአሁን ወቅት ኃይል ለማግኘት 60ሺ የሚጠጉ ከፍለው ለሚጠባበቁ ደንበኞች ችግር ለመፍታት የሚያስችል ነው፡፡

48417644 2291333844212049 5921565638282706944 n


Print