ከኤሌክትሪክ ጋር በተገናኘ ማድረግ ያለብን የጥንቃቄ ጉዳዮች

No automatic alt text available.

• ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ከአንድ ቤት ወደ ሌላ ቤት የሚዘረጋ የኤሌክትሪክ መስመር አደጋ ስለሚያስከትል ከዚህ ድርጊት መቆጠብ ያስፈልጋል!
• የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ሁልጊዜ በባለሞያ ብቻ መከናወን አለበት!
• ተበጥሶ መሬት ላይ የወደቀን ወይም የተንጠለጠለን የኤሌክትሪክ ሽቦ መንካት ለከፋ አደጋ ስለሚያጋልጥ መጠንቀቅ ያሻል!


• ውሀ ውስጥ፣ እርጥብ መሬትና ኤሌክትሪክ አስተላላፊ ነገር ላይ ቆሞ የኤሌክትሪክ መሳሪያዎቹን ከመንካት መቆጠብ አለብን!
• እንደሳታላይት ሪሲቨር፣ ቴሌቭዥን፣ ኮምፒውተር፣ ፋክስና የመሳሰሉት ዕቃዎች ተገጥመው ሥራ ላይ ከመዋላቸው በፊት ተገቢው የቃጠሎ መከላከያ እንዲኖራቸው ባለሞያዎችን ማማከር ያስፈልጋል! 
• የኤሌክትሪክ ምሰሶዎችን በመኪና በመግጨት በንብረትና በሰው ህይወት ላይ አደጋ እንዳይደርስ ተገቢውን የአሽከርካሪነት ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል!

በማንኛውም ቦታና ጊዜ የኤሌክትሪክ አደጋ የሚያስከትል ምልክት ካዩ ወዲያውኑ በቅርብ ከሚገኝ የአገልግሎት መስጫ ማዕከል ያሳውቁ ወይም ወደ 905 ነፃ ጥሪ ማዕከላችን ይደውሉ፡፡


Print