training2

ኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒንግ /ERP/………...

›› ተቋማችን ለደንበኞች የሚሰጠዉን አገልግሎት ዘመናዊ፣ ፈጣን፣ ቀልጣፋና ዉጤታማ ለማድረግ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት የትግበራ ፕሮግራም ቀርፆ ለመተግበር በመጨረሻዉ የዝግጅት ምዕራፍ ላይ ይገኛል፡፡

›› ትግበራዉ አለም አቀፍ ደረጃዉን በጠበቀ ሶፍትዌር በመታገዝ ደንበኞች ከተቋማችን የሚያገኙት አገልግሎት በተሻለ መልኩ ግልጽና ቀልጣፋ የሚያደርግ እንዲሁም ተደራሽነትን ለማቀላጠፍ ያግዛል፡፡

›› ይህንን በሚፈለገዉ ደረጃ ተግባራዊ የሚያደርጉ የተቋማችን ባለሞያዎች ስለ ኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒግ /ERP/ የአቅም ግንባታ ስልጠና በየደረጃዉ እየተሰጣቸዉ ነዉ፡፡