የኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒንግ (ERP) እና ተጓዳኝ የአይቲ መሰረተ-ልማት አቅርቦትና ትግበራ ፕሮጀክት የተቋሙን ገቢ አሰባሰብ፣ የፋይናንስ ስርዓት፣ የንብረት አያያዝ እና የሃብት አጠቃቅምን የሚመለከቱ ወቅታዊ የመረጃ ልውውጥ በማፋጠን አጠቃላይ የተቋሙን የውስጥ አሰራር ዘመናዊ በማድረግ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ለተገልጋይ ደንበኞች መስጠት የሚያስችል የአሰራር ስርዓት ነው፡፡ 

ፕሮጀክቱ የገንዘብ ዝውውር፣ የግዢ ስርዓት፣ንብረት አስተዳደርና የእቃ ግምጃ ቤት፣ የሰው ሃብት አስተዳደር፣ የፕሮጀክት አስተዳደር፣ የጥራት አስተዳደር፣ የደንበኞች አገልግሎት፣ ቢል፣ የገንዘብ አሰባሰብ፣ የደንበኛ አካውንት፣ የደንበኛ መረጃ አያያዝ፣ የቆጣሪ መረጃ አያያዝና አስተዳደር እና  የግንኙነት /የጥሪ ማዕከል/፣ ቋሚና ተለዋጭ የመረጃ  ቋት እና የመሳሰሉ  ዝርዝር ስራዎችን ለማከናወን የሚያስችል ነው፡፡

ፕሮጀክቱ በ9 የክልል ቢሮዎች እና በሁለት ከተማ መስተዳድሮች እንዲሁም ከ400 በላይ በሚሆኑ የአገልግሎት መስጫ ማዕከላትን በኢንተርኔትና ዳታ ኮሙኒዩኬሽን ኔትዎርክ በማገናኘት ግልጸኝነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት የአሰራር ስርዓት ነው፡፡   

ፕሮጀክቱ በሁለት ኮንትራት ተከፍሎ በመተግበር ላይ ያለ ሲሆን፡-

 1. የመጀመርያው ኮንትራት፡-
 • የኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒንግ (ERP) እና የአይቲ መሰረተ ልማት አቅርቦትና ትግበራ እንዲሁም አንድ አመት ዋራንቲ በአለም ባንክ ብድር ፋይናንስ የሚሰራ አጠቃላይ ወጪ 46.03 ሚሌዮን ዶላር ፡፡
 1. የሁለተኛው ኮንትራት፡-
 • የሦስት አመት ድህረ ዋራንቲ የጥገናና ድጋፍ አጠቃላይ ወጪ 12.86 ሚሌዮን ዶላር ሲሆን ፕሮጀክቱ በተቋሙ ዋና መስራ ቤት፣ በ9 የክልል ቢሮዎች እና ሁለት የከተማ አስተዳደር፣ ጎፋ ዋናው ዕቃ ግምጃ ቤት፣ ኮተቤ ወርክሾፕ እና ገራጅን ጨምሮ ከ400 በላይ የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት በመተግበር ላይ ይገኛል፡፡ ፕሮጀክቱ በ52 ቋሚ ሰራተኛ/ የሰው ኃይል የተደራጀ ነው፡፡

ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ የሚያስገኛቸው ጠቀሜታዎች

 • የተቋሙ የስራ ሂደቶች፣ ፕሮሲጀር፣ ማንዋልና አጠቃላይ የመረጃ አያያዝ፣ አጠቃቀም እና ልውውጥ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ /በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ እንዲሆን ያደርጋል፣
 • በማኑዋል የሚሰሩና ባልተቀናጀና ባልተደራጀ ሁኔታ የሚሠሩ ሥራዎችን ወደ አንድ ሲስተም/ሥርዓት እንዲገቡ በማድረግ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የታገዘ የሥራ ሂደት እንዲኖር ያደርጋል፣
 • ለሥራ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን የመሰብሰብ፣ የማጠናቀርና የመተንተን ስራዎችን በማቃለል እና የመረጃ ድግግሞሽን በማስቀረት የመረጃ አያያዝ እና አቅርቦት አስተማማኝ እንዲሆን ይረዳል፣
 • በተቋሙ ስር የሚገኙ የደንበኛ አገልግሎት መስጫ ማዕከላትን፣ የክልል ቢሮዋችን፣ እቃ ግምጃቤት፣ ጋራጅ እና ዎርክሾፕ፣ ዋናው መስራያ ቤት ጋር በኢንተርኔትና በዳታ ኮሚኒኬሽ ኔትዎርክ በማገናኘት የመረጃ ልውውጡን ወቅታዊ፣ ፈጣን፣ አስተማማኝ በማድረግ የተቋሙን ሃብት (ንብረት፤ገንዘብ እና ሙያተኛ) ውጤታማ በሆነ መልኩ ማቀድና መጠቀም ከማስቻሉ በተጨማሪ ፈጣን እና ፍትሃዊ የውሳኔ አሰጣጥ ስርዓት እንዲኖር ይረዳል፣
 • የተቋሙ ሰራተኛ ሲስተሙን ተጠቅሞ እንዲሰራ በማድረግ ምርታማነቱን እንዲጨምር ያደርጋ፣

   የፕሮጀክቱ ያለበት ደረጃ

የፕሮጀክቱ ዋና ዋና የትግበራ ስራዎች የፍላጎት ትንተና፣ ዲዛይን፣ ሪያላይዜሽን፣ ሙከራ እና ስልጠና በማጠናቀቅ የመጨረሻ ትግበራው (Go-Live) በተለያየ ደረጃ በመለየት በሂደት ላይ ይገኛል፡፡ የመጨረሻው ትግበራ (Go-Live) ያለበት ደረጃ ከታች እንደሚከተለው ተዘርዝሯል፡-

       የኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒንግ (ERP) ሞጅሎች

 1. I. ምዕራፍ አንድ (Phase I)

የኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒንግ (ERP) አጠቃላይ ሞጅሎች በሁሉም የተቋሙ ክፍሎች ከሚያዝያ 1/2011 ዓ.ም ጀምሮ ተተግብሯል፡፡

 • የፋይናንስና ቁጥጥር (FICA)
 • የሰው ሀብት (HCM)
 • ንብረት አስተዳደር (MM)
 • የፕሮጀክት አስተዳደር (PS)
 • ኢንተርፕራይዝ አሴት አስተዳደር (EAM)
 • የጥራት አስተዳደር (QM)
  1. II. ምዕራፍ ሁለት (Phase II)

ከደንበኞች አገልግሎት ጋር የተያያዙ አፕልኬሽኖች (Customer Centric Applications) ከግንቦት 22/ 2011 ዓ.ም ጀምሮ በአራቱም የአዲስ አበባ ዲስትሪክቶች ተተግብሯል፡፡

 • የደንበኞች አስተዳደር (CRM)
 • ቢሊንግ እና ኢንቮይስ (Billling & Invoicing)
 • የደንበኞች ኮንትራት አስተዳደር (FICA)
 • ዲቫይስ/ሜትር ማናጅመነት (DM)
  • III. ደረጃ ሶስት (Phase III)

ከላይ የተዘረዘሩት ከደንበኞች አገልግሎት ጋር የተያያዙ አፕልኬሽኖች (Customer Centric Applications) ከሐምሌ 01/ 2011 ዓ.ም ጀምሮ በ6 የክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ቢሮዎች (አማራ፣ ትግራይ፣ ቤንሻንጉል ጉምዝ፣ ጋምቤላ፣ ሃረሪ እና ድሬዳዋ) ለመተግበር በእቅድ ተይዞ እየተሰራ ይገኛል፡፡

 1. IV. ደረጃ አራት (Phase IV)

ከላይ የተዘረዘሩት ከደንበኞች አገልግሎት ጋር የተያያዙ አፕልኬሽኖች (Customer Centric Applications እና የደሲሽን ሰፖርት ሲስተም ሞጅሎች (BI/BW, MDAS) ከነሃሴ 01/ 2011 ዓ.ም ጀምሮ በቀሪዎቹ የክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ቢሮዎች (ኦሮምያ፣ ደቡብ፣ አሶሳ፣ ሶማሌ) ለመተግበር እቅድ ተይዞ እየተሰራ ይገኛል፡፡

 • በአጠቃላይ ፕሮጀክቱ አሁን ባለበት ሁኔታ 96% አፈጻጸም ደረጃ ላይ የደረሰ ሲሆን የተቋሙን የውስጥ አሰራር ዘመናዊ በማድረግ ለተገልጋዩ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት ግልጸኝነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት የአሰራር ስርዓት ለመዘርጋት ብሎም የተቋሙን የለውጥ ሂደት ተግባርዊ ለማድረግ ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ታውቆ በከፍተኛ ማኔጅመንቱ እንዲሁም ጉዳዩ በሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ክትትልና ድጋፍ እየተደረገለት ይገኛል፡፡