መንግስት በአሁኑ ወቅት ለዜጎች በቂ እና አስተማማኝ የስራ ዕድል ለመፍጠር እና  ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ ዕድገትን እውን ለማድረግ የሚያስችሉ የፖሊሲና የአሰራር ማሻሻያዎችን ተግባራዊ ለማድረግ እየሰራ ይገኛል።

 

EEu buliding picture

ፈርጀ ብዙ ገጽታ ያለውን የንግድና ኢንቨስትመንት ከባቢን አመችነትን በከፍተኛ ሁኔታ በመቀየር የሀገራችንን የእድገት ደረጃ በአጭር ጊዜ በማሻሻል ከመጀመሪያዎቹ 100 ሀገራት ተርታ እንድትገባ የሚያስችሉ ሰፊና አፋጣኝ የሪፎርም ስራዎችን መስራት ተገቢ እንደሆነ ታምኖበታል።

የዓለም ባንክ የ“ቢዝነስ አመቺነት”(Ease of Doing Business)የደረጃ ሰንጠረዥ ለማውጣት እንዲያስችለው ካስቀመጣቸው ወደ አስር የሚደርሱ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ምቹነት መለኪያዎች ውስጥ የኤሌክትሪክ አቅርቦት አንዱ እና ዋነኛው ነው።

የኤሌክትሪክ አቅርቦትን እንደ አንድ የቢዝነስ አመችነት ወይም የንግድ እና ኢንቨስትመንት ምቹነት መለኪያነቱ ለማሻሻል የዓለም ባንክ ያወጣቸው በአጭር፣ በመካከለኛ እና በረጅም ጊዜ መወሰድ ያለባቸው የመፍትሄ ተግባራትን ለማሳካት አሁን መሬት ላይ ያለውን የአሰራር ሂደት እና የሌሎች ሀገራትን ምርጥ ተሞክሮ ማወዳደር። እንዲሁም በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ የአጭር ጊዜ፣ የመካከለኛ ጊዜ እና የረጅም ጊዜ የመፍትሄ ተግባራትን በመለየት የማያስፈልጉ የስራ ሂደቶችን በማውጣት መሻሻል ያለባቸውን በማሻሻል ለየስራ ክፍሎች ተወካዮች ያሳውቃል።

በአጭር ጊዜ ተከናወኑት ተግባራት ውስጥ

  • የታሪፍ ማስተካከያውን ለአዲስ ደንበኛ በonline ማሳወቅ እና ቢል ከመታተሙ በፊት ፍጆታውን ለደንበኛው ማሳወቅ፡

              አዲሱ የታሪፍ ማስተካከያ በተቋሙ ድህረ ገጽ ላይ ተጭኗል፣፣

            ቢል ከመታተሙ በፊት ፍጆታውን ለደንበኛው ማሳወቅ፤ይህም ERP ተግባራዊ ሲደረግ በቅርቡ

           ወደ ስራ የሚገባ ይሆናል፣

  • ለአዲስ ደንበኛ ምዝገባ የሚያስፈልጉ ማስረጃዎች (Documents) መቀነስ፡

             አላስፈላጊ የሆኑ  ማስረጃዎችን (Documents)  በመቀነስ  እስከ 7.5 ኪ.ዋ ማመልከቻ ቅጽ እና መታወቂያ እንዲሁም 

            ከ7.5 ኪ.ዋ በላይ ለሆኑ ደንበኞች ማመልከቻ ቅጽ፣  መታወቂያ እና ኢንስታሌሽን ፕላን

  • ለሳይት ጉብኝት እና ዋጋ ግምትን በ5 የስራ ቀናት ውስጥ መፈጸም፡

              እስከ 150 ኪ.ዋ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ መፈጸም፣

             ከ150 ኪ.ዋ እስከ 3 ሜ.ቮ.አ. በ7 የስራ ቀናት ውስጥ መፈጸም፣

             ከ3 ሜ.ቮ.አ. እስከ 10 ሜ.ቮ.አ. በ10 የስራ ቀናት ውስጥ መፈጸም፣

             ከ10 ሜ.ቮ.አ. በላይ በ15 የስራ ቀናት ውስጥ መፈጸም፣

  • 10% የዋስትና ተቀማጭን ማስቀረት፡

            ቅድመ ክፍያ ቆጣሪዎችን በመጠቀም የዋስትና ተቀማጭን ማስወገድ፣ ለድህረ ክፍያ ቆጣሪ ተጠቃሚዎች

            የባንክ ክፍያን በመጠቀም ከ10 ሜጋ ዋት በላይ ተጠቃሚ ለሆኑ ደንበኞች የባንክ 

            ዋስትና(Bank Guarantee) በማስያዝ፣