አዲስ ኃይል ፈላጊ ደንበኞች ኃይል ለመጠየቅ ሲመጡ ሊያሟሏቸው የሚገቡ መስፈርቶች

metre2

 1. የአመልካቹን ማንነት የሚገልጽ የቀበሌ መታወቂ፣ ፓስፖርት፣ መንጃ ፍቃድ፣
 2. ለኃይል ማሻሻያ ወይም ለተጨማሪ ቆጣሪ የኤሌክትሪክ ፍጆታ የመጨረሻ ክፍያ ደረሰኝ፣
 3. በውክልና የሚተዳደር ቦታ ከሆነ በተራ ቁጥር አንድ የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ በተጨማሪ ህጋዊ የውክልና ሰነድ፣
 4. ቤት በመከራየት የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለማግኝት የሚፈልጉ አመልካቾች ከአከራይ የይሁንታ ማረጋገጫ ሲቀርቡ፣
 5. የሽርክና ድርጅት ከሆነ በተራ ቁጥር አንድ የተገለጸው እንዳለ ሆኖ ህጋዊ የሽርክና ማረጋገጫ ሰነድ ሲያቀርብ፣
 6. በመንግስታዊ አካል ለሚተዳደሩ ቤቶች እና ቦታዎች ውስጥ የሚኖሩ ተከራዮች በሁለት መንገድ ተጠቃሚ ይሆናሉ፣
  • ቤቱን በመንግስት ስም የተዋዋለ ተከራይ በሚመለከተው የመንግስት አካል ሲፈቅድ እና ተጠቃሚው ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ ሲቀርብ ቆጣሪይ ይፈቀድለታል፣ ማንኛውም ኃላፊነት ቤቱን የሚያስተዳድረው የመንግስት አአካል የሆናል፣
  • የመንግስት (የቀበሌ) ቤት ተከራይ የኪራይ ውል አያይዞ ሲያቀርብ ቆጣሪ በተከራይ ስም ሊያገኝ ይችላል፣ ለሚሰጠው ቆጣሪ ሙሉ ኃላፊነት የተከራይ ይሆናል፣
 7. ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት ከሆነ በተራ ቁጥር አንድ የተገለጸው እንዳለ ሆኖ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የዋና ስራ አስኪያጁ ማንነት የሚገልፅ መታወቂያ፣
 8. የሶስት ፌዝ ጠያቂ ደንበኞች ከሆኑ በባለስልጣን/የኤሌክትሪክ ነክ ፈቃድ ባለው ስራ ተቋራጭ የተሰጠ የውስጥ ኤሌክትሪክ መስመር ምርመራ መጠናቀቅ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አማካኝነት ተረጋገጦ ሲቀርብ፣

የአዲስ ኃይል አቅርቦት ማመልከቻ በተገለፀው መሠረት በሁሉም ጉዳዮች የተሟላና ከተተመነ የግምት ክፍያ ጋር (ካለ) ከተፈላጊ ሰነዶች ጋር በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ቢሮዎች በመገኝት ውል መፈፀም ይጠበቅባችዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለመላው ኢትዮጵያዊያን እንኳን ለ2012 አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ይገልፃል፡፡ny

ተቋማችን የሚሰጠውን አገልግሎት በቴክኖሎጂ የተደገፈ፣ ቀልጣፋና ጥራት ያለው እንዲሆን በርካታ ሥራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡

ከእነዚህ መካከል በተለይ ያረጁ የኤሌክትሪክ ማሰራጫ መስመሮችን የማሻሻልና ዓቅማቸውን የማሳደግ፣ የኃይል ብክነትን የመቀነስ፣ ለተቋሙ የመጀመሪያ የሆነ የራሱ ዘመናዊ የጥሪ ማዕከል አስገንብቶ አገልግሎት የመስጠት፣ የኔትዎርክ ኦፐሬሽን ለማቀላጠፍና አደጋን ለመከላከል የሬዲዮ መገናኛ ቴክኖሎጂ የመጠቀም፣ ተደራሽ ለመሆን አዳዲስ የኃይል ምንጭ አማራጮችን በመጠቀም ከዋናው የኤሌክትሪክ መረብ ውጪ የሚገኙ አካባቢዎችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ የማድረግ ሥራዎች ይጠቀሳሉ፡፡

ውድ ደንበኞቻችን እነዚህ የተጀመሩ ሥራዎችን በአዲሱ ዓመት በማጠናከር የእናንተን ዕርካታ በተሻለ መልኩ ለማሳደግ የምንሰራ መሆኑን እየገለፅን፤ መጪው ዘመን የሰላም፤ የፍቅርና የብልፅግና እንዲሆንላችሁ በድጋሚ እንመኛለን፡፡

መልካም አዲስ #ዓመት!
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

 

ALL SERVICE

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በዋናው መስሪያቤትና በስሩ በሚገኙ በሁሉም የመስተዳድርና የክልል ተጠሪ ቢሮዎች ነገ ቅዳሜ ጥቅምት 10 ቀን 2011 ዓ.ም ነፃ የሥራ ዘመቻ መርሃግብር ያካሂዳል፡፡

 

ALL SERVICE

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በዋናው መስሪያቤትና በስሩ በሚገኙ በሁሉም የመስተዳድርና የክልል ተጠሪ ቢሮዎች ነገ ቅዳሜ ጥቅምት 10 ቀን 2011 ዓ.ም ነፃ የሥራ ዘመቻ መርሃግብር ያካሂዳል፡፡

melkam siraተቋማችን በዋናው መስሪያቤትና በስሩ በሚገኙ በሁሉም የመስተዳድርና የክልል ተጠሪ ቢሮዎች ዛሬ ጥቅምት 03 እና በሚቀጥለው ሳምንት ጥቅምት 10 ቀን 2011 ዓ.ም ነፃ የሥራ ዘመቻ መርሃግብር እንደሚያካሂድ ትላንት ማሳወቃችን ይታወቃል፡፡