በአገራችን ኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ያለውን የሀይል ፍላጎት ከተለያዩ የኃይል ምንጮች ኃይል በማመንጨትና በማሰራጨት ለማመጣጠን የተደረገው ጥረት ከፍተኛ ቢሆንም አሁን ባለው የኤሌክትሪክ ታሪፍ መሰረት የሚሰበሰበው ገቢ በየወቅቱ እየጨመረ የመጣውን የህብረተሰብ የኤሌክትሪክ ኃይል ፍላጎት ጥያቄን መልስ ለመስጠት የሚያስችል ካለመሆኑም በላይ እየተሰጠ ያለውን አገልግሎት እንኳን ባለበት ሁኔታ ለማስቀጠል የሚያስችል አይደለም፡፡ በአሁኑ ወቅት ይህን ክፍተት በመጠኑም ቢሆን ለመሙላት በአራት አመታት ውስጥ የሚተገበር የኤሌክትሪክ ታሪፍ  ማስተካከያ  ከታህሳስ 1 ቀን 2011 ዓ.ም በአገር ዓቀፍ ደረጃ ተግባራዊ መደረግ ጀምሯል፡፡

          መደብ

ንዑስ መደብ

ከታህሳስ 2012 ጀምሮ

ዝቅተኛ ቮልቴጅ ኢንዱስትሪ (220 እና 380 ቮልቴጅ)

ነጠላ ታሪፍ

            1.0544              

ዲማንድ ቻርጅ

            100.00                       

መካከለኛ ቮልቴጅ ኢንዱስትሪ (15 ኬቪ)

ነጠላ ታሪፍ

            0.8008                         

ዲማንድ ቻርጅ

             73.77                            

ከፍተኛ ቮልቴጅ ኢንዱስትሪ ታሪፍ መደብ (ከ66 ኬቪ በላይ)

ነጠላ ታሪፍ

            0.6540                         

ዲማንድ ቻርጅ

             43.82                            

ማስተካከያው ከሚመለከታቸው የታሪፍ መደቦች መካከል የኢንዱስትሪ የታሪፍ መደብ አንዱ ስሆን በዚህ መደብ ከታህሳስ ወር 2012 ጀምሮ ለአንድ አመት ተግባራዊ የሚደረገው የታሪፍ ማስተካከያ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

የቀረበው በኢንዱስትሪ የታሪፍ መደብ ሶስት የታሪፍ መደቦችን ያካተተ ሲሆን እነርሱም ዝቅተኛ ቮልቴጅ ኢንዱስትሪ (220 እና 380 ቮልቴጅ) ፣ መካከለኛ ቮልቴጅ ኢንዱስትሪ (15 ኬቪ) እና ከፍተኛ ቮልቴጅ ኢንዱስትሪ ታሪፍ መደብ (ከ66 ኬቪ በላይ) ናቸው፡፡ በመሆኑም የኢንዱስትሪ ታሪፍ ደንበኞች የወርሃዊ ክፍያ መጠን የሚወሰነው በታሪፍ መደባቸው እና በሀይል አጠቃቀማቸው መሰረት ይሆናል፡፡

የኢንዱስትሪ ታሪፍ ተጠቃሚ ደንበኞች አራት አይነት ክፍያ ይከፍላሉ፡፡ የመጀመሪያው የሀይል ፍጆታ ክፍያ (energy consumption charge) ይባላል፡፡ ይህም የተጠቀሙት የሀይል ፍጆታ ሂሳብ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ዲማንድ ቻርጅ (demand /capacity charge) ይባላል፡፡ ይህ ክፍያ ለኢንዱስትሪ ደንበኞች አዲስ እና ደንበኞች በሚጠቀሙት በእያንዳንዱ ኪሎዋት ላይ የተቀመጠ ማባዣ ነው፡፡  ሶስተኛው የክፍያ ዓይነት ፓወር ፋክተር ሱር ቻርጅ (power factor sur charge) ይባላል፡፡ ይህ ክፍያ ተሻሽሎ በቀረበው የኢንዱስትሪ ታሪፍ መደቦች መሠረት ደንበኞች ወርሃዊ ፓወር ፋክተራቸው ከተቀመጠው ስታንዳርድ ማለትም ከ 0.9 በታች ሲወርድ በእያንዳንዱ በቀነሰበት መቶኛ መጠን ልዩነት በተመደበው የፓወር (ዲማንድ) ፍጆታ ክፍያ ምጣኔ መሠረት እንዲከፈል ይደረጋል፡፡ አራተኛው ክፍያ የአገልግሎት ክፍያ (service charge) ነው፡፡ ይህም ደንበኞች ለሚያገኙት አገልግሎት የሚከፍሉት ክፍያ ማለት ነው፡፡

የሀይል ፍጆታ ክፍያ (energy consumption charge) ፣ ዲማንድ ቻርጅ (demand /capacity charge) እና የአገልግሎት ክፍያ (service charge) የኢንዱስትሪ የታሪፍ መደብ ተጠቃሚ ደንበኞች ወርሃዊ ሂሳብ ውስጥ የማይቀሩ (Mandatory) ክፍያዎች ሆነው የሚካተቱ ናቸው፡፡ የፓወር ፋክተር ሱር ቻርጅ (power factor sur charge) ግን ከተቀመጠው ስታንዳርድ ፓወር ፋክተር ማለትም ከ0.9 በታች ሲሆን ብቻ የሚከፍሉ ይሆናል፡፡

ለኢንዱስትሪ ደንበኞች የሀይል ፍጆታ ክፍያ ወጥ ታሪፍ (flat rate) እንዲሆን የተደረገ ሲሆን ቀድሞ የነበረው የዝቅተኛ (minimum charge) ክፍያ ታሪፍ ቀርቷል፡፡ በምትኩም የደንበኞችን ከፍተኛ የኃይል ጭነት (maximum demand) መሠረት በማድረግ የዲማንድ ቻርጅ (demand charge) ክፍያ ታሪፍ ተግባራዊ ሆኗል፡፡

የሁሉም የታሪፍ መደብ ደንበኞች ወርሃዊ የፍጆታ ሂሳብ የሚሰላው የደንበኛውን የሀይል አጠቃቀም መሰረት በማድረግ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በታሪፍ ማስተካከያው መሰረት የፓወር ፋክተር ሱር ቻርጅ (power factor sur charge) ክፍያ የሚሰላው በዲማንድ ቻርጅ ክፍያ ተባዝቶ መሆኑን የኢንዱስትሪ ደንበኞች ሊያውቁት ይገባል፡፡ በመሆኑም ደንበኞች ወርሃዊ የኃይል ፍጆታ ክፍያቸውን ተመጣጣኝ ለማድረግ የኃይል አጠቃቀማቸው ቁጠባን መሰረት ያደረገ መሆን ይኖርበታል፡፡

ለዚህም ደንበኞች የሪአክቲቭ ፓወራቸውን መቀነስ እንዲሁም የፓወር ፋክተር መጠናቸውን ማሻሻል ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህን ዕውን ለማድረግ ፓወር ፋክተር ኮሬክተር የሚባል መሳሪያ አገልግሎት ላይ ማዋል ጠቀሜታው የጎላ ነው፡፡ ፓወር ፋክተር ኮሬክተር የሚባክን ሀይል (reactive energy) ጥቅም ላይ ወደሚውል ሃይል (active energy) መቀየር የሚያስችል መሳሪያ በመሆኑ የኢንዱስትሪ ታሪፍ ደንበኞች በቂ ሀይል በማግኘት የፍጆታ ሂሳባቸውን ለመቀነስ ብሎም ውስን የሆነውን የአገር ሀብት በቁጠባ ለመጠቀም ያስችላቸዋል፡፡

በመሆኑም የኤሌክሪክ ሀይልን በቁጠባ በመጠቀም ወጪን እንቀንስ!