የኤሌክትሪክ ታሪፍ ማስተካከያ

የኤሌክትሪክ ታሪፍ ማስተካከያ

ከታህሳስ 1 ቀን 2011 ዓ.ም በፊት ስራ ላይ የነበረው የኤሌክትሪክ ታሪፍ ከአስራ ሁለት ዓመታት በላይ ማስተካከያ ሳይደረግለት የቆየ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይህ ታሪፍ እየጨመረ ከመጣው አገራዊ የኤሌክትሪክ ኃይል ፍላጎት፣ የደንበኛ ብዛት፣ ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ፍላጎት አንፃር ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠትና ለማስፋፋት የሚያስችል ገቢ ሊያስገኝ አልቻለም፡፡ በመሆኑም በኤሌክትሪክ ኃይል ልማትና አቅርቦት ዘርፍ ከሚደረገው ግዙፍ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴና ከሚያስፈልገው ተጨማሪ የኢንቨስትመንት ፍላጎት አንጻር ከዘርፉ የሚገኘው ገቢ የተሟላ አገልግሎት ለመስጠት በሚያስችል መጠን ሊስተካከል እንደሚገባ ታምኖበታል፡፡tarfi11

በታሪፍ ማስተካከያው ጥናት ግኝት መሰረት ከማገዶ እንጨት በስተቀር የታሪፍ ማስተካከያው ለቤት ውስጥ ምግብ ማብሰያነት እና ለብርሃን ሰጪነት  ከሚውሉ ሌሎች የሀይል አማራጮች አንፃር የኤሌክትሪክ ኃይል ተወዳዳሪ እንደሆነ ተረጋግጧል፡፡ በተለይ ለመኖሪያ ቤት አገልግሎት ሲባል በመጀመሪያው እርከን ላይ የተቀመጠው 50 ኪሎዋት ሰዓት በወር የድጎማ ታሪፍ በመሆኑ እጅግ አዋጪ ነው፡፡ በቀጣዩ እርከን ላይ ያለው እስከ 100 ኪሎዋት ሰዓት በወር እንዲሁ በጣም የተሻለና በአብዛኛው የተደጎመ አማራጭ ነው፡፡ በሶስተኛው እርከን ላይ የተመላከተው እስከ 200 ኪሎዋት ሰዓት በወር በከፊል በድጎማ የተካተተበት የታሪፍ ዕርከን ነው፡፡ በአጠቃላይ የታሪፍ አወቃቀሩ የኢነርጂም ሆነ የሃይል  ፍጆታ ቁጠባን እንደሚያበረታታ ይጠበቃል፡፡ ይህም ለአቅርቦት አስተማማኝነት የራሱ  ድርሻ ይጫወታል፡፡

የታሪፍ ማስተካከያው በተጠቃሚ አይነትና በኢነርጂ ሜትር (ቆጣሪ) አይነት መሰረት ቀርቧል፡፡ በዚህ መሰረት የመኖሪያ ቤት (ከደረጃ 1 እስከ ደረጃ 7)፣ አጠቃላይ (የአገልግሎት ተቋማት/ ሰርቪስ ሴክተር)፣ ኢንዱስትሪ (ዝቅተኛ፣ መካከለኛና  ከፍተኛ)፣ የጅምላ ሽያጭ ታሪፍ በሚል ተለይቷል፡፡ የአገልግሎት ክፍያ ደግሞ በቅድመ አገልግሎትና ድህረ አገልግሎት (ለመኖሪያ ቤትና አጠቃላይ) እና ባለ ሶስት ፌዝ (ለኢንዱስትሪ) በሚል እንዲዘጋጅ ተደርጓል፡፡ ስለሆነም የተቋሙ ደንበኞች በታሪፍ መደባቸው መሰረት ከታች በቀረበው መረጃ መሰረት ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታና የአገልግሎት ክፍያ ስሌታቸውን በቀላሉ መረዳት ይችላሉ፡፡

 1. የመኖሪያ ቤት ደንበኛ ነዎት?

የመኖሪያ ቤት ደንበኞች የታሪፍ ማስተካከያ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

 • የመኖሪያ ቤት ታሪፍ

የመኖሪያ ቤታችን የኤሌክትሪክ ኃይል አጠቃቀምና ፍላጎት በመጠንም ሆነ በአይነት ከአገራዊ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ዕድገት ጋር ተያይዞ እያደገ መጥቷል፡፡ የአንድ ማህበረሰብ የኃይል ፍላጎት መጨመር ተፈጥሮአዊ ዕድገት መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ የአገልግሎት ጥያቄ አቅራቢው ህብረተሰብ ለአቅርቦቱ (supply) ቀጣይነትና አስተማማኝነት የበኩሉን ድርሻ መወጣት ይጠበቅበታል፡፡

 • የመኖሪያ ቤት ታሪፍ ማስተካከያ ሰባት ዕርከን ያለው ሲሆን የመጀመሪያዎቹ ሶስት እርከኖች በተለያየ ደረጃ ድጎማ እንዲደረግባቸው ተደርጓል፡፡
 • አዲሱ የክፍያ አሠራር በቀድሞው የታሪፍ ዕርከን መሰረት ሁሉም ተጠቃሚዎች በየእርከኑ ያለውን ታሪፍ በመደመር የሚከፍሉበት ሳይሆን ሙሉ የፍጆታ መጠን በሚያመለክተው እርከን ላይ ያለውን ታሪፍ ብቻ በመጠቀም የሚከፍሉበት አሠራር ነው፡፡

           የመኖሪያ ቤት የአራት አመት የታሪፍ ማስተካከያ

መደብ

ንዑስ መደብ

 ወርሃዊ ፍጆታ (ኪዋሰ)

የተግባር ዘመን

ከታህሳስ 2011 ጀምሮ በኪዋሰ (በብር)

ከታህሳስ 2012 ጀምሮ በኪዋሰ (በብር)

ከታህሳስ 2013 ጀምሮ በኪዋሰ (በብር)

ከታህሳስ 2014 ጀምሮ በኪዋሰ (በብር)

መኖሪያ ቤት

1ኛ ብሎክ

እስከ 50

      0.2730

  0.2730

0.2730

0.2730

2ኛ ብሎክ

እስከ 100

0.4591

0.5617

0.6644

0.7670

3ኛ ብሎክ

እስከ 200

0.7807

1.0622

1.3436

1.6250

4ኛ ብሎክ

እስከ 300

0.9125

1.2750

1.6375

2.0000

5ኛ ብሎክ

እስከ 400

0.9750

1.3833

1.7917

2.2000

6ኛ ብሎክ

እስከ 500

1.0423

1.4965

1.9508

2.4050

7ኛ ብሎክ

ከ500 በላይ

1.1410

1.5877

2.0343

2.4810

የመኖሪያ ቤት ታሪፍ የአገልግሎት ክፍያ

በፍጆታ ላይ የተመሰረተው የቀድሞው ባለ ስድስት እርከን ክፍያ ቀርቶ ሁለት እርከን ያለው የአከፋፈል ስርዓት ስራ ላይ እንዲውል ተወስኗል፡፡ ክፍያውም በኢነርጂ ሜትር (ቆጣሪ) አይነት ማለትም በቅድመ እና በድህረ አገልግሎት አይነት መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

የታሪፍ መደብ

የፍጆታ መጠን

/አይነት/

ክፍያ (በብር)

መኖሪያ ቤት

ድህረ አገልግሎት እስከ 50 ኪዋሰ

10.00

ድህረ አገልገሎት ከ50 ኪዋሰ በላይ

42.00

ቅድመ አገልግሎት እስከ 50 ኪዋሰ

3.50

ቅድመ አገልግሎት ከ50 ኪዋሰ በላይ

14.70

 1. ጠቅላላ ታሪፍ መደብ ደንበኛ ነዎት?

የጠቅላላ መደብ ታሪፍ ደንበኞች የታሪፍ ማስተካከያ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

2.1 ጠቅላላ ታሪፍ መደብ

 • ቀድሞ የነበረው በሁለት እርከን ላይ የተመሠረተው የጠቅላላ ታሪፍ መደብ የድጎማ የኢነርጂ ታሪፍ ቀርቶ በነጠላ ታሪፍ (Flat) ታሪፍ እንዲተካ ተደርጓል፡፡ የጠቅላላ ታሪፍ መደብ እንደቀድሞው ሁሉ በተቀሩት የታሪፍ መደብ ውስጥ ሊካተቱ የማይችሉት ተገልጋዮች የሚካተቱበት መደብ ነው፡፡
 • የጎዳና (የመንገድ) መብራት በአገልግሎት ወጪ በኩል ከሌሎች በጠቅላላ ታሪፍ መደብ ውስጥ ከተካተቱት የማይለይ በመሆኑ ሌላ ለብቻ የሆነ የታሪፍ መደብ ሳያስፈልገው በአጠቃላይ የታሪፍ መደብ ውስጥ እንዲስተናገድ ሆኗል፡፡

የጠቅላላ ታሪፍ መደብ የአራት አመት የታሪፍ ማስተካከያ

መደብ

ንዑስ መደብ

ወርሃዊ ፍጆታ (ኪዋሰ)

                የተግባር ዘመን

ከታህሳስ 2011 ጀምሮ በኪዋሰ (በብር)

ከታህሳስ 2012 ጀምሮ በኪዋሰ (በብር)

ከታህሳስ 2013 ጀምሮ በኪዋሰ (በብር)

ከታህሳስ 2014 ጀምሮ በኪዋሰ (በብር)

ጠቅላላ ታሪፍ መደብ

ነጠላ ታሪፍ

-

1.0352

1.3982

         

        1.7611

      2.1240

የጠቅላላ ታሪፍ መደብ የአገልግሎት ክፍያ

የጠቅላላ መደብ የአገልግሎት ክፍያን በቅድመ ክፍያ እና በድህረ ክፍያ ቆጣሪ አይነት ተለይቶ ተግባራዊ እንዲሆን ተደርጓል፡፡

የታሪፍ መደብ

የፍጆታ መጠን /አይነት/

     ክፍያ (በብር)

 አጠቃላይ ታሪፍ መደብ

ድህረ አገልግሎት

      54.00

ቅድመ አገልግሎት

      18.90

ጅምላ ሽያጭ ታሪፍ

በአዲሱ የኤሌክትሪክ ዘርፍ አደረጃጀት መሠረት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ራሣቸውን የቻሉ ተቋማት በመሆናቸው ታሪፉ እስኪስተካከል ድረስ ለጊዜው የ40-60 ገቢ ክፍፍል እንዲኖራቸው በሥራ አመራር ቦርድ ተወስኖ በሥራ ላይ ውሎ ነበር፡፡ ይህን የገቢ ክፍፍል በማስቀረት የኤሌክትሪክ ኃይል አመንጪው ለአከፋፋይና ለቸርቻሪው በጅምላ የሚያቀርቡበትን ዋጋ መተመን አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ የጅምላ ታሪፍ ክፍያ ሥርዓት ተግባራዊ እንዲሆን ተደርጓል፡፡ በተከናወነው የታሪፍ ማስተካከያ ጥናት የማመንጫ የኢነርጂ ወጪ እና የማስተላለፊያ የኃይል /አቅም/ ዲማንድ ወጪ ላይ የተመሠረተ ታሪፍ የተካተተ ሲሆን ሁለቱንም አይነት ክፍያዎች የያዘ ታሪፍ ተግባራዊ ሆኗል፡፡

                    ጅምላ ሽያጭ የአራት አመት ታሪፍ ማስተካከያ

መደብ

ንዑስ መደብ

ወርሃዊ ፍጆታ (ኪዋሰ)

የተግባር ዘመን

ከታህሳስ 2011 ጀምሮ በኪዋሰ (በብር)

ከታህሳስ 2012 ጀምሮ በኪዋሰ (በብር)

ከታህሳስ 2013 ጀምሮ በኪዋሰ (በብር)

ከታህሳስ 2014 ጀምሮ በኪዋሰ (በብር)

የጅምላ ሽያጭ ታሪፍ

ወርሃዊ የማስተላለፊያ ታሪፍ በኪዋሰ

-

 39.2908

78.5815

117.8723

157.1600

ማመንጫ ታሪፍ

-

0.2218

0.4435

0.6553

0.8870

 1. የከፍተኛ ሀይል ተጠቃሚ ደንበኛ ነዎት?

የከፍተኛ ሀይል ደንበኞች የታሪፍ ማስተካከያ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

 • የኢንዱስትሪ ታሪፍ

የኢንዱስትሪ ተገልጋዮች የታሪፍ ተመን  ወጥ ሆኖ የተዘጋጀ ሲሆን በቀድሞው የታሪፍ መደብ የነበረው ነገር ግን ሥራ ላይ ያልዋለው የከፍተኛ ኃይል ጭነት እና የዝቅተኛ ኃይል ጭነት ታሪፍ (ሚኒመም ቻርጅ) ተሰርዟል፡፡ በተጨማሪም የዝቅተኛ ኃይል ታሪፍ አከፋፈል እንዲቀር የተደረገ ሲሆን በምትኩ የኢንዱስትሪ ደንበኞች የኃይል (Power) ክፍያ እንዲካተት ተድርጓል፡፡ የኃይል ክፍያ ቀደም ሲል ያልነበረ ቢሆንም በቀድሞው የታሪፍ ስሌት መሰረት በከፍተኛ ጭነት ክፍያ ውስጥ ይካተታል ተብሎ ታሣቢ ተደርጎ ነበር፡፡ ነገር ግን ክፍያው ተግባራዊ ባለመደረጉ ምክንያት የኃይል አቅርቦቱን ለማሳለጥ የሚያስፈልጉ የአገልግሎት ወጪዎችን ባለው አከፋፈል ለመሽፈን ሳይቻል  ቀርቷል፡፡ ወጪን በተሻለ ሁኔታ ለመሸፈንና ሸማቹም የኃይል አጠቃቀሙ ቁጠባን መሰረት ያደረገ እንዲሆን ለማስቻል ዓለም አቀፍ አሠራርን መሰረት በማድረግ ይህ የታሪፍ አሰራር ተግባራዊ እንዲሆን ተደርጓል፡፡

 • የሪአክቲቨ ፖወር አጠቃቀም ክፍያ በቀድሞው አሠራር መሰረት እንዲቀጥል ተደርጓል፡፡ በኢንዱስትሪ ታሪፍ መደቦች ውስጥ ተሻሽሎ በቀረበው መሠረት ወርሃዊ ፓወር ፋክተራቸው ከ90% በታች ሲወርድ በወረደበት መጠን ልክ በእያንዳንዱ በቀነሰበት መቶኛ መጠን ልዩነቱ በተመደበው የፖወር (ዲማንድ) ፍጆታ ክፍያውን ምጣኔ እንዲከፈል ይደረጋል፡፡
 • በዚህ የታሪፍ መደብ ስር ሆነው የሃይል ፍላጎታቸው ከ25 ኪዋ በላይ የሆኑት ሁሉ ለዝቅተኛ፣ለመካከለኛ እና ለከፍተኛ ቮልቴጅ ኢንዱስትሪ በተቀመጠው የታሪፍ መደብ ከላይ በተገለፀው የፓወር ፋክተር ስሌት መሰረት እንዲከፍሉ ይደረጋል፡፡
 • የዚህ መደብ የታሪፍ ማስተካከያ ወጥ ታሪፍ (flat rate) እንዲሆን የተደረገ ሲሆን በቀድሞው የታሪፍ መደብ የነበረው ነገር ግን በሥራ ላይ ያልዋለው ታሪፍ ተሰርዟል፡፡
 • የዝቅተኛ ታሪፍ አከፋፈል እንዲቀር የተደረገ ሲሆን በዚህ ምትክ የኃይል (demand) ክፍያ በወርሃዊ ከፍተኛ ኃይል (ማክሲመም ዲማንድ) የኃይል (KW) አጠቃቀም ላይ ተመሥርቶ የቀረበው አሠራር የኃይል ተጠቃሚዎች (ከ25 ኪዋ በላይ የሚያስፈልጋቸው) ከኢነርጂ ታሪፍ በተጨማሪ የኪሎዋት ታሪፍ የሚከፍሉበት አሠራር ተግባራዊ ተደርጓል፡፡

የኢንዱስትሪ የአራት አመት የታሪፍ ማስተካከያ

መደብ

ንዑስ መደብ

ወርሃዊ ፍጆታ (ኪዋሰ)

የተግባር ዘመን

ከታህሳስ 2011 ጀምሮ በኪዋሰ (በብር)

ከታህሳስ 2012 ጀምሮ በኪዋሰ (በብር)

ከታህሳስ 2013 ጀምሮ በኪዋሰ (በብር)

ከታህሳስ 2014 ጀምሮ በኪዋሰ (በብር)

ዝቅተኛ ቮልቴጅ ኢንዱስትሪ

ነጠላ ታሪፍ

-

0.8161

1.0544

1.2927

1.5310

ዲማንድ ቻርጅ

-

50.00

100.00

150.00

200.000

መካከለኛ ቮልቴጅ ኢንዱስትሪ (15 ኬቪ)

ነጠላ ታሪፍ

-

0.6047

0.8008

0.9969

1.1930

ዲማንድ ቻርጅ

-

36.8850

73.77

110.655

147.540

ከፍተኛ  ቮልቴጅ

ኢንዱስትሪ ታሪፍ

መደብ (ከ66 ኬቪ በላይ)

ነጠላ ታሪፍ

-

0.5174

0.6543

0.7911

0.9280

ዲማንድ ቻርጅ

-

21.9100

43.8200

65.730

  87.640

የኢንዱስትሪ ታሪፍ የአገልግሎት ክፍያ

ማንኛውም የኢንዱስትሪ ወይንም ባለ ሶስት ፌዝ ቆጣሪና የድህረ አገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኛ በወር 54 ብር የአገልግሎት ክፍያን እንዲከፍል የሚደረግ ሲሆን የኢንዱስትሪ ባለ ሶስት ፌዝ ቆጣሪና የቅድመ አገልግሎት ተጠቃሚ የሆነ ደንበኛ ደግሞ በወር 18.90 ብር የሚከፍል ይሆናል፡፡

የታሪፍ መደብ

የአገልግሎት አይነት

የፍጆታ መጠን /አይነት/

ክፍያ (በብር)

 ማንኛውም ኢንዱስትሪ

ድህረ ክፍያ

    ሶስት ፌዝ

54.00

ቅድመ ክፍያ

    ሶስት ፌዝ

18.90

ደንበኞች እንዴት የፍጆታ ሒሳባቸውን ማወቅ ይችላሉ?

ከላይ በሠንጠረዥ እንደሚታየው የመኖሪያ ቤት የታሪፍ ስሌት 7 ደረጃ (እርከን) ሲኖረው አንድ ደንበኛ የተጠቀመው በወር ኪ.ዋ.ሰ በሚያርፍበት መደብ ሁሉም ኪ.ዋ.ሰ በቀጥታ ተባዝቶ እንዲከፍል ይደረጋል፡፡

ለምሳሌ አንድ ደንበኛ በወር 250 ኪ.ዋ.ሰ ፍጆታ ቢጠቀም የሚሰላበት እርከን በቀጥታ 4ኛ መደብ ላይ ሆኖ በብር 0.9125 ተባዝቶ (250 x 0.9125 = 228.125) ሲሆን፤

የአገልግሎት ክፍያ ብር 42.00 ጨምሮ በድምሩ ብር 270.125 አጠቃላይ የፍጆታ ሂሳብ ይሆናል፡፡

በመኖሪያ ከምንጠቀምባቸዉ የኤሌክትሪክ  ቁሳቁሶች ከኃይል መጠን በመነሳት ፍጆታ ስሌት ብንመለከት ለምሳሌ አንድ ደንበኛ በመኖሪያ ቤታቸዉ ለብርሃን አገልግሎት ብቻ የሚጠቀሙበት 2 ባለ 60 ዋት ኤሌክትሪክ ጉልበት ያለዉ አምፑል ቢኖራቸዉ  እና በቀን 6 ሰዓት ቢጠቀሙ፤ አንድ የኤሌክትሪክ ምጣድ 3000 ዋት የሆነ በሦሰት  በሦስት ቀን  ለተከታታይ  2 ሰዓት ቢጠቀሙ በአጠቃላይ በወር የኤሌክትሪክ ፍጆታቸዉ እንደሚከተለው ይሆናል፤

አምፑል 2 X 60ዋት x 6 ሰዓት x 30 ቀናት = 21,600 ዋት ሰ

3000 ዋት x 2 ሰዓት x 10 ቀናት =   60,000 ዋት ሰ

                          ድምር 81,600 ዋት

 ወደ ኪዋት ሰዓት ሲቀየር 81.6 ኪ.ዋት ሰዓት

 የሚከፈልበት እርከን 2ተኛ በ 0.4591 x 81.6 ብር 37.46256

 የአገልግሎት ክፍያ ብር 42.00

 ጠቅላላ ድምር ብር 79.46 የፍጆታ ሒሳብ ይሆናል ማለት ነው፡፡


Print