የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት በመላ ሃገሪቱ ለሚገኙ 144 ሺህ 388 ኤስ.ቲ.ኤስ ቆጣሪዎችን ለደንበኞቹ አድርሷል፡፡ ከነዚህ ውስጥ 137 ሺህ 247 ያህሉ የነጠላ ፌዝ ተጠቃሚ ደንበኞች ናቸው፡፡

የኤስ.ቲ.ኤስ ቆጣሪዎች ከዚህ ቀደም ካሉት ቆጣሪዎች የሚያደርጋቸው ደንበኞች በተዘረጉት የክፍያ አማራጮች /በቴሌ ብር፣ በሞባይል ባንኪንግ፣ በሲ.ቢ.ኢ ብር፣ በኢንተርኔት ባንኪግ፣ በአዋሽ ብር ፕሮ፣ ኮፔይ ኢ-ብር እና ኤምፔሳ ሳፋሪኮም በጊዜና በቦታ ሳይወሰኑ የኤሌክትሪክ ኃይል መግዛት የሚያስችላቸው መሆኑ ነው፡፡

ከተገጠሙት ቆጣሪዎች መካከል ሲም ካርድ ያላቸውም ጭምር በመኖራቸው አላስፈላጊ የቆጣሪ ንክኪ ሲፈጠር መልዕክት ወደ ሲስተም በመላክ ተገቢውን እርምጃ ለመውሰድ የሚያግዙ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ናቸው፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ እነዚህን ቆጣሪዎችሚጠቀሙ ደንበኞች የኃይል መቋረጥ ቢገጥማቸው አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠትም የሚያግዙ ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በቴክኖሎጂ የተደገፈ ቀልጣፋና ምቹ አሰራር ለመዘርጋት በትኩረት እየሰራ የሚገኝ ሲሆን፣ ከተቋሙ ዘመናዊ የአሰራር ማሻሻያዎች መካከል አንዱና ዋናው በአገሪቱ እየተተገበረ የሚገኘው ዘመናዊ የኤስ.ቲ.ኤስ (STS) ቆጣሪ ቴክኖሎጂ ነው፡፡