የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከተጣለበት ሀገራዊ ኃላፊነት ባሻገር ማኅበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት በተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች ለሚገኙ የገቢ አቅማቸው ዝቅተኛ ለሆኑ ወገኖች ድጋፍ እያደረገ ነው፡፡
ተቋሙ በ2019 በጀት ዓመት መጀመሪያ ሩብ ዓመት ብቻ ከ1.8 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የተለያዩ ድጋፎችን አድርጓል፡፡
ከ875 ሺህ ብር በላይ በሆነ ወጪ ከ10 ሺህ በላይ የመማሪያ ደብተሮችን በአዲስአበባ፣ ድሬደዋ፣ ሀረር፣ ነቀምቴ፣ ትግራይ፣ ሶማሌ፣ አፋርና ደቡብ ኢትዮጵያ ለሚገኙና ድጋፍ ለሚሹ ተማሪዎች አበርክቷል፡፡
በተያያዘ በአርባምንጭ፣በወላይታ ሶዶ እንዲሁም አፋር በተቋሙ አመራሮችና ሠራተኞች ተሳትፎ ከ150 ሺህ ብር በላይ የሚገመት የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጓል፡፡ ይህም ተማሪዎች ትምህርታቸውን በተሻለ ሁኔታ እንዲከታተሉ እገዛ አድርጓል፡፡
ለጌርጌሴኖን የአእምሮ ህሙማን መርጃና ማገገሚያ ማዕከል በ681 ሺህ ብር የምግብ፣ የአልባሳትና የንፅህና መጠበቂያ ግብዓቶች ስጦታ፤ በ137 ሺህ ብር ወጪ ደግሞ ከ20 ሺህ በላይ ችግኝ ተከላ ተከናውኗል፡፡
በተጨማሪም በተቋሙ በጎ ፈቃደኛ አመራሮችና ሠራተኞች ተሳትፎም 39 ዩኒት ደም ተለግሷል፡፡
በዚህም በአጠቃላይ ተቋሙ በሩብ ዓመቱ ከ1.8 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ በማድረግ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ተወጥቷል፡፡
CommunityNOV 14, 2026 · By EEU Communications Team · 1 min read
ተቋሙ ከ1.8 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ማህበራዊ ድጋፍ አደረገ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ማኅበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት በ2019 በጀት ዓመት መጀመሪያ ሩብ ዓመት ብቻ ከ1.8 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ልዩ ልዩ ድጋፎችን አድርጓል።



